Description
"ጌታችሁ የሰፊ ችሮታ ባለቤት ነው። . . ." - ቁርዓን 6፡147
ኃያሉ አላህ ለፍጥረተ ዓለሙ በፍቅርና በደግነት የተሞላ ነው። በዚህኛውም ሆነ በቀጣዩ አለማት ያሉ ችሮታዎችና መልካምነቶች የእዝነቱ ግልፅ ማረጋገጫዎች ናቸው።
በእርግጥም አላህ ለእኛ ከገዛ እናቶቻችን የበለጠ አዛኝ መሆኑን እስልምና ያስተምራል።
ታዲያ ከዚህ የተለየ ምን ሊሆን ይችላል፥ አንዳንድ የአላህ መልካም ስሞች እና ንፁህ ባህሪያት ቀጣዮቹን የሚያካትቱ ሆነው ሳለ፤
• ንስሐ ተቀባዩ፤
• ሩህሩሁ፤
• የውዴታው ባለቤት፤
• ታጋሹ፤
• እጅግ ሩህሩሁ፤
• እጅግ አዛኙ፤
• የበጎነት ምንጩ፤
• እጅግ ቸሩ፤
• ሁሉን ሰጪው፤
እነዚህ ስሞች ሁሉም አላህ በእዝነት፣ በበጎነትና በቸርነት ባህሪያቱ እንደሚገለፅ ያሳያሉ።
መላ ፍጥረተ አለሙ ላይ የሚያወርደውን እዝነቱን ስፋትና ምሉዕነት ይመሰክራሉ።
ይህንኑ ፍጥረት አላህ እንዲህ ሲል ጥሪ ያደርግለታል፥ “የአደም ልጅ ሆይ፥ ምድርን የሚሞላ ኃጢአት ሰርተህ ወደኔ ብትመጣና ከፊቴ ብትቆም፥ በኔ ላይ ሌላን እስካላጋራህ ድረስ፥ ምድርን የሚሞላ ምሕረት ላቀርብልህ እችላለሁ።”
የአላህ እዝነትና በረከት ምሳሌዎች
"ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?" - ቁርዓን 55፡13
መልካም ጤንነትም ይባል ማየት፣ መስማት፣ ምግብ፣ ንፁህ አየር፣ ልጆች፣ ሐብት እና ሌሎች ተቆጥረው የማያልቁ ነገሮች፥ ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ያለማቋረጥ የአላህ በረከት ይደርሳቸዋል።
አንዳንዶች ከአላህ የተቸሯቸውን የማስተዋልና የማሰብ ስጦታዎች በመጠቀም እነዚህን በረከቶች አመስግነው ይቀበላሉ፤ የህይወት አላማቸውን ይጨብጣሉ፤ በዚያውም ራሳቸውን ለአላህ ያሳድራሉ።
ነገር ግን ሌሎች ደግሞ አላህ ለእነሱ ስላደረገላቸው እዝነት ግድ አይሰጣቸውም - እሱን የካዱ ሆነው ሳለ እየመገባቸውና እያኖራቸው እንኳ።
ምንም እንኳ ፍጥጥ ብለው እሱን ቢክዱትም፥ የእንቅስቃሴ፣ ዘና የማለት፣ የሐሳብ እና የድርጊት ነጻነት ተሰጥቷቸዋል።
በአላህ እዝነት ቢሆን እንጂ፥ ከናካቴው አይኖሯትም ነበር።
በአጠቃላይ፥ ሁሉም ሰው የተሰጡትን በረከቶች አመስግኖ የመቀበል፣ አላህ (የሰው ልጆች ጌታ) ባዘዘው መልኩ የመጠቀምና እርሱን ብቻ የመገዛት ነፃ ምርጫው አለው።
እኚህን መሰል በረከቶች ከዚህ በታች በጨረፍታ ጠቃቅሰናቸዋል፤ ምክንያቱም “ . . . የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም። አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና።" - ቁርዓን 16፡18
ከመለኮት በተላኩ መጻሕፍትና ነቢያት መመራት
"ከርሱ በፊት ያሉትን መጻሕፍት የሚያረጋግጥ ሲሆን መጽሐፉን (ቁርዓንን) ባንተ ላይ (ሙሐመድ ሆይ) ከፋፍሎ በእውነት አወረደ። ተውራትንና ኢንጂልንም አውርዷል።" - ቁርዓን 3፡3
ከተፈጠረ ጀምሮ፥ የሰው ልጅ የህይወትን ውጣ ውረድ እንዲጋፈጥ ለብቻው አልተተወም ነበር። በአላህ እዝነት፥ የሰው ልጅ በነቢያት በኩል ራዕይ ደርሶታል፤ ነብያትም ህዝቦቻቸው ለመምራትና ለመጠበቅ ራዕይን ያደረሱና ያስተማሩ ናቸው።
ከራዕዮች ሁሉ እጅግ ምሉዕ እና በእዝነት የተሞላው ቅዱስ ቁርዓን ሲሆን የነብያቱ ማክተሚያ ደግሞ ሙሐመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ነበሩ።
ቁርዓን – የመጨረሻው መለኮታዊ መፅሐፍ – የቀደሙትን መፃህፍት የተካና የሻራቸው ሲሆን ለሰው ዘር የወረደ ታላቁ እዝነት እና መመሪያ ነው።
በቀደሙት ዘመናት አላህ መልእክተኞችን እንደላከው ሁሉ፥ የቁርዓን የእዝነትና የፍትህ አስተምህሮቶች እንዴት በቀን ተቀን ህይወታችን ውስጥ በተጨባጭ መተግበር እንዳለባቸው የሚያሳየንን ህያው፣ ምሉዕ እና ተግባራዊ ምሳሌ አክሎ ለሰው ልጅ ልኳል።
ይህ ምሳሌ፥ ለሰው ልጆች እዝነት ሆነው የተላኩት ነቢዩ ሙሃመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ነበሩ።
"(ሙሐመድ ሆይ!) ለዓለማትም እዝነት አድርገን እንጂ አልላክንህም።" - ቁርዓን 21፡107
ቀጣዮቹ ጥቅሶች፥ አዛኝነታቸውን፣ ደግነታቸውን፣ ታጋሽነታቸውን እና ውብ አስተምህሮታቸውን የሚጠቁሙ አንዳንድ የነብዩ ንግግሮች ናቸው።
· "ደግነት በምንም ነገር ውስጥ አይገኝም ነገርዬው ውበቱን የሚጨምርለት ቢሆን እንጂ፤ ከምንም ነገር ውስጥ አይታጣም ነገርዬው የሚያኮሥሠው ቢሆን እንጂ።”
· "ከአማኞች መካከል በእምነቱ እጅግ ምሉዕ የሆነው በባህሪው እጅግ ምርጥ የሆነው ነው።"
· "ጎረቤቱ ተርቦ ሳለ እርሱ ጠግቦ የሚያድር ሙሉ ሙስሊም አይደለም።"
· "ለሌሎች የማያዝን አላህ አያዝንለትም።"
እኛ እንደ ማህበረሰብ፥ ደግሞም በእነዚህ ጊዜያት፥ መሰል ማራኪ ምክሮች እንዴት የምር እንደሚያስፈልጉን?
ለፍጥረተ ዓለሙ ስለማዘን
የሰው ልጆች መፈጠርም ሆነ የተሰጧቸው ችሎታዎች በሙሉ በራሳቸው ትልቅ እዝነት ናቸው።
ከእንቅልፍ መነሳት፣ ሥራ መስራት፣ መመገብ፣ መጫወትና መተኛት መቻላችን አመስጋኞች ሊያደርገን ይገባል።
“ከችሮታውም ለእናንተ ሌሊትንና ቀንን በውስጡ ልታርፉበት፣ ከትሩፋቱም ልትፈልጉበት፣ አመስገኞችም ልትሆኑ አደረገላችሁ።" - ቁርዓን 28፡73
የትዳር አጋር፥ ስክነትንና ፍቅርን ማግኛ መንገድ፥ ከታላላቅ እዝነቶች መካከል አንዱ ነው።
"ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ።" - ቁርዓን 30፡21
ከሐጢዓት የነፃን አድርጎ መፍጠሩና ለአካለ መጠንና የማመዛዘን እድሜ ላይ እስክንደርስ ተይዘን የማንጠየቅ የመሆናችን ተጨባጭ ሌላ እዝነት ነው።
ይህ ከክርስትና "የውርስ ኃጢአት" ፅንሰ ሐሳብ ጋር ሙሉ በሙሉ የሚቃረን ነው።
ኃጢአትን ይቅር ማለት የአላህ እዝነት ሌላ ምሳሌ ነው፤ ፍፁም አለመሆናችንንና ስህተቶችን እንደምሰራ አላህ ያውቃልና።
አማኞች ሐጢዓት ሰሪ የመሆናችን ተጨባጭ ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ አለብን አልያም የአላህን ይቅርታ ጨርሰንበታል ማለት አይደለም።
"እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ። አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና። እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና።" - ቁርዓን 39፡53
እንስሳት እንኳ ከአላህ እዝነት የተወገዱ አይደሉም። እነርሱ የመስማትና የማየት ችሎታዎች አሏቸው፤ ምግብና ዘር ያገኛሉ፤ እንዲሁም ሌሎች ብዙ በረከቶች ተሰጥተዋቸዋል።
እነርሱ ሰማኝነትና እይታ ይኖራቸዋል፤ መንግሥት፣ ልጆች እና ሌሎች በረከቶችም ይሰጣሉ።
ወደምድር በወረደችው የአላህ እዝነት አንዷ ክፍል የተነሳ እዝነቱ ሁሉንም ያካብባቸዋል።
"...የእሱ ፍጡራን እርስ በርሳቸው ይተዛዘናሉ፤ በዚህም የተነሳ ፈረስ እንኳ አራስ ጨቅላዋን በሸኾናዋ እንዳልረግጠው ብላ ከመሬት ደግፋ ታስነሳዋለች።”
አዛኙ ፈጣሪ እያንዳንዱ ፍጡር እንክብካቤ ማግኘቱን ያረጋግጣል - ውቅያኖስ ሆድ ውስጥ ከሚዋኙ አሳዎች በምድር ላይ እስከሚርመሰመሱ ነፍሳት ብሎም በሰማይ እስከሚበሩ አዕዋፋት ድረስ ሁሉም በእርሱ ተረዛቂዎች ናቸው።
የአላህን እዝነት በእኛ ላይ እንዴት ማሳደግ እንደምንችል
“የአላህ ችሮታ ለበጎ አድራጊዎች ቅርብ ነውና።" - ቁርዓን 7፡56
በቀጣዩ አንቀፅ እንደተገለፀው፥ በእዝነቱ የተነሳ፥ ትክክለኛውን መንገድ ለተከተለ ሁሉ ይቅርታና ምህረት እንደሚያደርግ አላህ ቃል ገብቷል።
"እኔም ለተጸጸተ፣ ላመነም፣ መልካምንም ለሠራ፣ ከዚያም ለተመራ ሰው በእርግጥ መሓሪ ነኝ።" - ቁርዓን 20፡82
የመጨረሻውን መልዕክተኛ፥ ሙሃመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን)፥ ማመንና መታዘዝ ትክክለኛ እምነት የመያዝ የማይነጠል አካል ነው።
በአጭሩ፥ የአላህን እዝነት በብዛት የሚያገኙት ለእርሱ በረከቶችና ውለታዎች እውቅና የሰጡ፣ አላህን በሚያስደስት መልኩ የተጠቀሙባቸው፣ አላህ የሰጣቸውን ሐብት እርዳታ ላይ ያዋሉና ችግረኞችን የተንከባከቡ፣ ለየቲሞች (እናት አባት ለሌላቸው) የድጋፍ እጃቸውን የዘረጉ፣ የንግግር ተስጥዖዋቸውን መልካምን ለመናገር የተጠቀሙ፣ እንዲሁም አላህ ያዘዛቸውን ሌሎች ክቡር ተግባራት የፈፀሙ ሰዎች ናቸው።
ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ አሉ፥ "ለሰዎች እዝነትን ለሚያሳዩ ሰዎች አላህ እዝነቱን ያሳያል። ምድር ላይ ለሚኖሩት እዘኑ - የሰማዩ አንድዬ ያዝንላችኋልና።"
ከታች የቀረቡት፥ የአላህን እዝነት ማግኛ አንዳንድ መንገዶች ናቸው።
"ይታዘንላችሁም ዘንድ አላህንና መልክተኛውን ታዘዙ።" - ቁርዓን 3፡132
በቁርዓን ውስጥ የሚገኙትን የእዝነትና የፍትህ አስተምህሮቶች በመከተል፥ "ይህም ያወረድነው የሆነ የተባረከ መጽሐፍ ነው። ተከተሉትም። ይታዘንላችሁም ዘንድ (ከክህደት) ተጠንቀቁ።" - ቁርዓን 6፡155
"ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ። ምጽዋትንም ስጡ። መልክተኛውንም ታዘዙ።ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና።" - ቁርዓን 24፡56
ከአላህ ዘንድ እዝነትን ከልብ መለመን። «ጌታችን ሆይ! ቅኑን መንገድ ከመራኸን በኋላ ልቦቻችንን አታዘምብልብን። ከአንተ ዘንድ የሆነን ችሮታም ለኛ ስጠን። አንተ በጣም ለጋስ ነህና።» - ቁርዓን 3፡8
እዝነትና ተጠያቂነት
ከአላህ የአዛኝነት ባህርይ ጎን ለጎን የፍትሐዊነት ባህሪውም አለ።
አላህ እጅግ በጣም አዛኝ ነው፤
"ለጥንቁቆቹ በጌታቸው ዘንድ መጠቀሚያ ገነቶች አሏቸው። ሙስሊሞቹን እንደ ከሓዲዎች እናደርጋለን? ለእናንተ ምን (አስረጅ) አላችሁ? እንዴት ትፈርዳላችሁ?" - ቁርዓን 68፡34-36
ግን ደግሞ እርሱ ምርመራው ፈጣን ነው።
አንድ ሰው አላህን ማታለል ሊሞክርና ያለልባዊ ፀፀት አልያም ወደዚያ ወንጀል መቼም ላለመመለስ ሳይቆርጥ ተመሳሳይ ሐጢዓቶችን በቋሚነት በመፈፀም የአላህን እዝነት ያላግባብ ሊጠቀም አይችልም።
"ጸጸትንም መቀበል ለእነዚያ ኀጢአቶችን ለሚሠሩ አንዳቸውንም ሞት በመጣበት ጊዜ ‘እኔ አሁን ተጸጸትኩ’ ለሚልና ለነዚያም እነርሱ ከሓዲዎች ሆነው ለሚሞቱ አይደለችም።" - ቁርዓን 4፡18
ሙስሊሞች ለመልካም ስራዎቻቸው ሽልማት አገኛለሁ ብለው ተስፋ እንዲያደርጉ፥ ለሚፈፅሟቸው ኃጢዓቶች ደግሞ ቅጣት አለብኝ ብለው እንዲጨነቁ ይበረታታሉ።
ኃጢአቶችን በሚፈፅሙ ጊዜ፥ ከልብ በመፀፀት ምህረት እንደሚያገኙ ተስፋ ያደርጋሉ።
እናም በመጨረሻ፥ በፈጣሪያቸው ቃል ይብቃቃሉ፤ ብሎም ወደልቦቻቸው አስጠግተው ይይዙታል፤
“አላህ ለሰዎች በእርግጥ ሩኅሩኅ አዛኝ ነው፡፡" - ቁርዓን 22፡65
