የሴቶች መብት በእስልምና حقوق المرأة فى الإسلام

3.95 MB 104 1 Files
albyan
or download free
[free_download_btn]

Description

የተከበረች። የተወደሰች። የተወደደች።

መግቢያ

በእስልምና ውስጥ ሴቶች እንደታሰሩ፣ እንደተዋረዱ እና እንደተጨቆኑ ይታሰባል - የምር ግን ነገሩ እንዲያ ነው?

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች እንዲሁ እንደቀላል ያን ያህል ጨቋኞች ቢሆኑ ነው ወይስ እነዚህ የተሳሳቱ እይታዎች አድሏዊ በሆነ ብዙሃን መገናኛ የተፈበረኩ ናቸው?

"ለእነርሱም (ለሴቶች) የዚያ በእነርሱ ላይ ያለባቸው (ግዳጅ) ብጤ በመልካም አኗኗር (በባሎቻቸው ላይ መብት) አላቸው።" ቁርዓን 2፡228

በምዕራቡ ዓለም ያሉ ሴቶች ገና በቅርቡ ማጣጣም የጀመሯቸውን መብቶች እስልምና ከአንድ ሺህ አራት መቶ ዓመታት በፊት ለሴቶችን መብቶችን ሰጥቷል።

በ1930ዎቹ፥ አኒ ቤሳንት ይህን አስተውላለች፥ "ገና በመጨረሻዎቹ 20 ዓመታት ነው ክርስቲያናዊት እንግሊዝ ሐብት የማፍራት መብትን ለሴቶችን የፈቀደችው፤ እስልምና ይህን መብት በሁሉም ዘመናት ፈቅዶ ኖሯል።

እስልምና ሴቶች ነፍስ እንደሌላቸው ይሰብካል ብሎ መውቀስ ባዶ ሐሜት ነው የሚሆነው።" - (የሙሀመድ ሕይወት እና አስተምህረቶች፣ 1932)

ወንዶችና ሴቶች ሁሉም ከአንድ ሰው የተገኙ ናቸው - ከነቢዩ አደም (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን)።

እስልምና ለሁለቱም ፆታዎች ከፍትሐዊነት እና ከመልካም አያያዝ ውጪ ምንም ሊላ ነገር አይቀበልም።

እኩል ሽልማት እና እኩል ተጠያቂነት

ወንዶችና ሴቶች በአንድ አይነት መንገድ አላህን ያመልካሉ፤ ማለትም ተመሳሳይ አምላክን (አላህ) ያመልካሉ፣ ተመሳሳይ የአምልኮ ተግባራትን ይፈፅማሉ፣ በተመሳሳይ መጽሐፍ ይመራሉ፣ ተመሳሳይ እምነት አላቸው።

አላህ (የፍጥረተ ዓለሙ ሁሉ አንድዬ አምላክን የሚወክል አረቢኛ ቃል) ሁሉንም የሰው ልጆች በሚዛናዊነተና በእኩልነት ይዳኛል።

አላህ የሴቶችንም የወንዶችንም ያዘጋጀውን ፍትሐዊ ምርመራና ምንዳ ቁርዓን ውስጥ በብዙ አንቀፆች አስምሮበታል።

"አላህ ምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በመኖሪያ ገነቶችም ውስጥ መልካም መኖሪያ ቤቶችን ቃል ገብቶላቸዋል።" - ቁርዓን 9፡72

"እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው።" ቁርዓን 3፡195

እነዚህ አንቀጾች ምንዳ ማግኘት በፆታ ላይ ሳይሆን ጥገኛነቱ በስራ ላይ መሆኑን ያሳያሉ።

የሰው ልጅ እንዴት እንደሚመነዳና እንደሚዳኝ በመወሰን ረገድ ፆታ ምንም የሚጫወተው ሚና የለውም።

እስልምናን ከሌሎች ሃይማኖቶች ጋር ብናነፃፅረው፥ በጾታዎቹ መካከል ፍትሕን እንደሚያስጠብቅ እናያለን።

ለምሳሌ፥ ከተከተከለው ዛፍ ለመብላታቸው ሐዋን ከአደም ይበልጥ ተወቃሽ የማድረግን ሐሳብ እስልምና ውድቅ ያደርጋል።

እንደ እስልምና አተያይ፥ አደምም ሐዋም ሐጢአት ሰርተዋል፤ ሁለቱም ተፀፅተው አላህ ምሯቸዋል።

የእውቀት እኩል መብት

ወንዶችና ሴቶች እውቀትን እንዲፈልጉ በእኩል ተበረታትተዋል።

ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥"ትምህርት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው።"

እንዲሁም በነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘመንና በአቅራቢያቸው ታላላቅ ሴት ሙስሊም ምሁራን ኖረዋል።

አንዳንዶቹ ከቤተሰባቸው መሃል ሌሎቹ ደግሞ ሶሃቦቻቸው ወይም የእነርሱ ሴት ልጆች ነበሩ።

ከእነርሱ ውስጥ የነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ባለቤት ስመ ገናናዋ አዒሻ ነበረች፤ አንድ አራተኛ የሚሆነው ኢስላማዊ ሸሪዓ (ህግ) በእርሷ አማካይነት ነው የተላለፈው።

ሌሎች ሴቶች ደግሞ ታላላቅ የፊቅህ ሊቃውንት የነበሩ ሲሆን ዝነኛ ወንድ ምሁራን ተማሪዎቻቸው ነበሩ።

ውሃ አጣጪን የመምረጥ እኩል መብት

እስልምና ውሃ አጣጪን የመምረጥ እኩል መብት በመስጠት እና ካገቡም በኋላ የመጀመሪያውን የቤተሰብ ስማቸውን ይዘው እንዲቆዩ በመፍቀድ ሴቶችን አክብሯል።

በተጨማሪም፥ ወላጆች ሴቶች ልጆቻቸውን ለትዳር እንደሚያስገድዷቸው አይነት ስሜት ብዙዎች አላቸው። እንደሚግድ ይታሰባሉ።

ይህ ባህላዊ ዘልማድ ሲሆን፥ ኢስላማዊ መሰረት የለውም።

ይህ እንዲያውም ክልክል ነው።

በነቢዩ ሙሀመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘመን አንዲት ሴት ወደ እርሳቸው ቀርባ እንዲህ አለች፥ "አባቴ ማኅበራዊ ደረጃውን ከፍ ለማድረግ ብሎ ለአጎቴ ልጅ አስገድዶ ያለኔ ፍላጎት ድሮኛል።"

ነቢዩም ወደልጂቱ አባት መልዕክተኛ ልከው አስጠሩትና ልጂቱን በእሱ ፊት እንዳገባች መቆየትን ወይም የትዳሩን መሰረዝ ምረጪ አሏት።

እርሷም፥ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ፥ አባቴ የመረጠልኝን ተቀብያለሁ፤ ነገር ግን ሌሎች ሴቶችን (ወደጋብቻ ተገደው መግባት እንደሌለባቸው) ለማሳየት ፈልጌ ነው።” አለች።

እኩል ግን የተለያዩ

ወንዶችና ሴቶች እንደ አጠቃላይ መርህ እኩል መብቶች ቢኖሯቸውም፥ የተሰጧቸው ተናጥላዊ መብቶችና ሃላፊነቶች ግን አንድ አይነት አይደሉም።

ወንዶችና ሴቶች ተገዳዳፊ መብቶችና ኃላፊነቶች አሏቸው።

ከውጫዊ እና ውስጣዊ አካላዊ ልዩነቶች ባሻገር፥ የሴቶችና የወንዶች አንጎሎች፥ ከብዙ በጥቂቱ ለመዘርዘር፥ እንደቋንቋ፣ መረጃ እና ስሜት የመሳሰሉ ጉዳዮችን በሚያካሂዱበት ስልት ሌሎች በርካታ ረቂቅ ልዩነቶች በመካከላቸው መኖራቸውን ሳይንቲስቶች ያውቃሉ።

የሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲው የማህበረ ስነህይወት ሊቅ ኤድዋርድ ኦ. ዊልሰን ሴቶች በአንደበታዊ ክህሎት፣ በርህራሄ እና በማህበራዊ ክህሎት፥ ሌሎች ነገሮችንም ጨምሮ፥ ከወንዶች የመብለጥ አዝማሚያ እንደሚያሳዩ፥ እንዲሁም ወንዶች በአንፃሩ ራስን በመቻል፣ በቦታና ሂሳባዊ ክህሎት፣ ከደረጃ ጋር በተያያዘ ነውጥ፣ ብሎም በሌሎች ጠባዮች ከሴቶቹ የመብለጥ ነገር እንደሚያሳዩ ተናግረዋል።

ሁለቱንም ጾታዎች ተመሳሳይ አድርጎ መውሰድ እና ልዩነታቸውን ችላ ማለት ሞኝነት ነው የሚሆነው። እስልምና ወንዶችና ሴቶች ተደጋጋፊ፥ ግን ደግሞ የተለያዩ፥ ሚናዎች እንዳሏቸው ያስተምራል፤ ምክንያቱ ካኸላለቃቸው ጋር ይበልጥ የሚስማማ በመሆኑ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፥

"...ወንድም እንደ ሴት አይደለም።" - ቁርዓን 3፡36

"የፈጠረ አምላክ እርሱ ዕውቀት ረቂቁ፣ ውስጥ ዐዋቂው ሲኾን (ምስጢርን ሁሉ) አያውቅምን?" - ቁርዓን 67፡14

ቤተሰብ በአንድነት

አላህ ወንዶችንና ሴቶችን፥ ከየራሳቸው ሚናዎች፣ ክህሎቶች እና ሐላፊነቶች ጋር የተለያዩ አድርጎ ፈጥሯቸዋል።

እነዚህ ልዩነቶች የሚታዩት የበላይነት ወይም የበታችነት ማስረጃ ተደርገው ሳይሆን እንደ ሙያ ክፍፍል ነው።

በእስልምና ውስጥ ቤተሰብ ማእከላዊ ጠቀሜታ አለው።

ወንዱ የቤተሰቡ የፋይናንስ ደህንነት ሐላፊነት አለበት፤ ሴቷ ደግሞ ለቤተሰቡ አካላዊ፣ አስተዳደጋዊ (ትምህርት) እና ስሜታዊ ደህንነት አስተዋፅዖ ታደርጋለች።

ይህም ከፉክክር ይልቅ ትብብርን ያበረታታል።

በመተሳሰብና በእርስበርሳቸው ሳምንቶች እንደነበር ቤተሰቦችን እና ወገኖችን ታላቅ ያላቸው አይሰባሰቡም።

እንዲሁም በስሜት ደረጃ፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች አንዳቸው ያላንዳቸው ደስተኛ ህይወት አይኖሩም። አላህ ይህን ውብ አርጎ እንዲህ ይገልፀዋል፤

"እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለነርሱ ልብሶች ናችሁ።" - ቁርዓን 2፡187

ልብስ ምቹነትን፣ ሙቀትንና ደህንነትን ይሰጣል፤ ብሎም ጥሩ መስህብ እንዲኖር ያደርጋል፤ በዚህ መልኩ ነው እንግዲህ በባልና ሚስት መካከል ያለን ግንኙነት እስልምና የበየነው።

በባልና በሚስት ግንኙነት ውስጥ ፍቅር እና መተዛዘን

ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በተጨማሪም ወንዶች ሚስቶቻቸውን በምርጥ አያያዝ እንዲይዟቸው አበረታትተዋል፥ "ከእናንተ መሐል ምርጦቹ ለሚስቶቻቸው (በአያያዝ) ምርጥ የሆኑት ናቸው።"

"ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ።" - ቁርዓን 30፡21

አኢሻ (የነቢዩ ሚስት) በአንድ ወቅት ቤት ውስጥ የነቢዩ ጠባይ እንዴት እንደሆነ ተጠይቃ ነበር።

እርሷም እንዲህ አለች፥ "እናንተም በቤታችሁ የምታደርጉትን ነው የሚያደርጉት፥ ብቻ ግን እጅግ ልዝብ እና እጅግ ደግ ናቸው ... በቤት ውስጥ የተለመዱ ተግባራት ሚስቶቻቸውን ያግዛሉ፤ የሚለብሱትን ልብስ ራሳቸው ይሰፋሉ እንዲሁም ጫማቸውን ይጠግናሉ።” በአጠቃላይ፥ ሚስቶቻቸው በሚሰሩት ስራ ሁሉ ያግዟቸው ነበር።

የእናቶችና የሴት ልጆች ከፍተኛ ደረጃዎች

እናት በልጅ ላይ በተለይም በመጀመሪያዎቹ የለጋነት ዓመታት በውዴታዋ፣ በእንክብካቤዋ እና በፍቅሯ አማካይነት እጅግ ከፍተኛ ተፅዕኖ አላት።

ያለ ምንም ጥርጥር፥ የማህበረሰብ ስኬታማነት በእናቶች የተነሳ ነው።

ስለዚህ፥ እነርሱን ማክበርና ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ ለእስልምና ትክክለኛው ነገር ነው።

አላህ በቁርዓን ውስጥ እንዲህ ይላል፦

"ሰውንም በወላጆቹ በጎ መዋልን በጥብቅ አዘዝነው። እናቱ በችግር ላይ ሆና አረገዘችው። በችግርም ወለደችው።" - ቁርዓን 46፡15

ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) በአንድ ወቅት እንዲህ ተጠየቁ፥ "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ፥ ከሰዎች ሁሉ መልካምነቴ የሚገባው ለማን ነው?"

እርሳቸውም፥ "እናትህ" አሉት።

ሰውዬው ሁለት ጊዜ፥ "ቀጥሎስ ማን ነው?" ሲል ጠየቀ። ተመሳሳይ መልስ ተሰጠው።

ነቢዩ ልክ በአራተኛው ነው "ቀጥሎ አባትህ" ሲሉ የመለሱለት።

እናቶችን በመልካምነትና በደግነት ለመንከባከብ ብቻ አይደለም ምንዳ የሚሰጠው። እንዲያውም፥ እስልምና ወንዶች ልጆችን በማሳደግ የማይገኝ ሴቶች ልጆችን በማሳደግ ብቻ የሚገኝን ልዩ ምንዳ አስቀምጧል።

ነቢዩ ሙሀመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥ "አላህ ሁለት ሴት ልጆችን ሰጥቶት ለእነርሱ መልካም የሆነላቸው፥ ለእርሱ ወደ ጀነት መግቢያ ምክንያት ይሆኑለታል።"

ማጠቃለያ

ከእስልምና በፊት፥ ሴቶች አሳፋሪ ተደርገው ይታዩ ነበር፤ ሴት ልጆችም ከእነ ህይወታቸው ይቀበሩ ነበር፤ ሴተኛ አዳሪነት ቅጥ አልነበረውም፤ ፍቺ ሙሉ በሙሉ በባል ብቻ እጅ ውስጥ ነበር፤ ውርስ ለጠንካሮች ብቻ ነበር፤ እንዲሁም ጭቆና ተንሰራፍቶ ነበር።

እስልምና መጥቶ እኚህን ልማዶች ጠራርጎ አጠፋ። በዛሬው ዘመን እንኳ፥ “በበለፀጉት አገራት”፥ ሴቶች ለእኩል ስራ እኩል ክፍያ ይቅርና፥ ተገቢው አክብሮት፣ ክብር እና ሞገስ አላገኙም።

እስልምና፥ ግን፥ ሴቶችን ውድ እና ዋጋ ያላቸው ያላቸው አድርጎ ነው የሚያያቸው ክብር ሊነፈጉም ሆነ ሊዋረዱ አይፈቅድም።

በአንዳንድ የመካከለኛው ምስራቅ ሐገራት ወይም ሙስሊም ቤተሰቦች ውስጥ ሴቶች ላይ የሚደርሰው በደል፥ በእስልምና ምክንያት ሳይሆን፥ አንዳንድ ሙስሊሞች በስህተት በሚከተሏቸው ባህላዊ ልማዶች የተነሳ ነው።

እስልምና ጨቋኝ ከሆነ፥ ታዲያ ለምንድን ነው በአለም ዙሪያ በርካታ ሴቶች በፈቃዳቸው ወደሐይማኖቱ የሚገቡት?

በጌታችን እና በጌታዎ፥ የሁሉም ወንዶችና ሴቶች ፈጣሪና አዋኝ በሆነው፥ ቃላት እንቋጫለን።

"ሙስሊሞች ወንዶችና ሙስሊሞች ሴቶች፣ ምእምናንና ምእምናትም፣ ታዛዦች ወንዶችና ታዛዦች ሴቶችም፣ እውነተኞች ወንዶችና እውነተኞች ሴቶችም፣ ታጋሾች ወንዶችና ታጋሾች ሴቶችም፣ አላህን ፈሪዎች ወንዶችና አላህን ፈሪዎች ሴቶችም፣ … አላህ ለእነርሱ ምሕረትንና ታላቅን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡" - ቁርዓን 33፡35

Similar Downloads

No related download found!