Description
እንዳለመታደል፥ በርካታ ሙስሊሞች ሰላት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እየተረዱ ወይ አይሰግዱም ወይ ደግሞ ቅድመ ሁኔታዎቹን አያሟሉም።
የሰላት ዓላማ ከአላህ ጋር ያሎትን ግንኙነት ማጠናከር፣ ለሰጠዎት ፀጋዎች ማመስገን፣ እና የእሱን ታላቅነት ራስዎን ማስታወስ ነው።
ልክ ሥጋ እንደ ምግብና ውሃ ያሉ አካላዊ ግብዓቶች እንደሚፈልገው ሁሉ፥ ነፍስም የሚያለመልሟትና መንፈሳዊ ፍላጎቶቿን የሚሞሉላት የአምልኮ ተግባራት የምትፈልግ ሲሆን ሰላት ደግሞ እጅግ በጣም አስፈላጊው ነው።
ሰው በአካላዊ ሁኔታው ጤናማ ሆኖ በመንፈሳዊ ሁኔታው ግን በድን የሚሆንባቸው ጊዜያት አሉ።
ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥ "አላህን በሚያስታውስና በማያስታውስ መካከል ያለው ልዩነት ሕያው በሆነና በሞተ መካከል እንዳለው አይነት ነው።"
አላህ እንዲህ ይላል፥
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! (መልክተኛው) ሕያው ወደሚያደርጋችሁ እምነት በጠራችሁ ጊዜ ለአላህና ለመልክተኛው ታዘዙ።" - ቁርዓን 8፡24
አስፈላጊነቱ
ከአላህ ጋር በቀጥታ መገናኘት
"አንድ ሰው ወደጌታው እጅግ የሚቀርበው በሱጁድ ጊዜ ነው።"
ሰላት ከአላህ ጋር ያገናኞታል።
አስ-ሰላህ የሚለው የአረቢኛ ቃል በእርግጥ "ግንኙነት" የሚል ፍች ከሚሰጥ የአረቢኛ ቃል የተመሰረተ ነው።
የአላህ መልእክተኛ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥ "ከእናንተ ማናችሁም ለሰላት ሲቆም፥ ከጌታው ጋር እየተነጋገረ ነው፤ ስለዚህ ከጌታው ጋር እንዴት እንደሚነጋገር ልብ ይበል።"
ከፈጣሪዎ ጋር ያሎትን ይህን ግንኙነት አያበላሹት።
የእስልምና አንድ ምሰሶ
ሰላት ሁለተኛው እጅግ አስፈላጊ የእስልምና ምሰሶ ነው፤ እንዲሁም በሙስሊም ህይወት ውስጥ እጅግ መደበኛው የግዳጅ (ፈርድ) ተግባር ነው።
ሰላት በየዕለቱ መፈፀም ያለበት ተግባር ነው - መቼቱ ምንም ይሁን ምን።
በመሰረቱ፥ አላህ ሙስሊሞችን በጦርነት ላይ ሆነው እንኳ ሰላትን አልተወላቸውም።
እንዲህ ይላል፥
“በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ።... ብትፈሩም እግረኞች ወይም ጋላቢዎች ሆናችሁ (ስገዱ)።" - ቁርዓን 2፡238-239
ጉዳዩ በጦርነት መሃል እንኳ እንዲህ ነው። ታዲያ በሰላም ጊዜ ምን ሊሆን ይችላል?
ስኬት በሰላት ውስጥ ነው
ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥ "ማንኛውም ሰው የትንሳኤ ቀን ከስራዎቹ በመጀመሪያ የሚመረመረው ከሰላቱ ነው።
ሰላቱ የተስተካከለ ከሆነ፥ ደህነኛና ስኬታማ ይሆናሉ።
ሶላቱ የተበላሸ ከሆነ፥ እድለ ቢስና ከሳሪ ይሆናል።”
ጠቀሜታዎቹ
ከክፉ ነገር ይከልላል
የአላህን እገዛ ሳይከጅሉ፥ ከክፉ ስራ መጠበቅ አይቻልም።
አላህ እንዲህ ይላል፥
"ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና።..." - ቁርዓን 29፡45
በቀን 5 ጊዜ አላህ ፊት ለመቆም ፈቃደኛ ከሆኑ፥ እንዴት ኃጢዓቶች ሊፈፅሙ ይቻልዎታል?
ነፍስዎን ያለመልማል
ሰላት ከፈጣሪዎ ጋር የመገናኘት መንፈሳዊ ፍላጎትዎን ያረካሎታል።
ይህም፥ በተለይም በዚህ የተጨናነቀ የሕይወት ዘይቤዎ፥ ነፍስዎን ሰላምና መብቃቃት ይሰጣታል።
አላህ እንዲህ ይላል፥
"ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ።" - ቁርዓን 13፡28
ትሑት ያደርገዎታል
የአላህን ታላቅነትና በእርሱ ላይ ጥገኛ መሆንዎን በመገንዘብ ኩራት እና ትዕቢት ይወገዳሉ።
በሰላት ውስጥ፥ ሙስሊም የአካሉን ከፍተኛውን ክፍልና የማስተዋል ምንጭ የሆነውን ጭንቅላቱን በመሬት ላይ በመድፋት እንዲህ ይላል፥ "ጌታዬ ምንኛ ፍፁም ነው፤ እጅግ የላቀው።"
እርሱ እንዲህ ይላል፣
"ምእምናን ፍላጎታቸውን ሁሉ በእርግጥ አገኙ (ዳኑ)።እነዚያ እነርሱ በስግደታቸው ውስጥ (አላህን) ፈሪዎች።" - ቁርዓን 23፡1-2
በእርግጥ ይህን ማሳካት የሚቻለው፥ የሚነበበውን መረዳት ሲችሉና በመተናነስ ሙሉ ትኩረትዎን ሲሰበስቡ ብቻ ነው።
ኃጢዓትን ያጥባል
ሁሉም ሰው ኃጢአትን ይሠራል፤ ነገር ግን፥ አላህ በሰላት አማካይነት፥ እነዚያን ኃጢአቶች ማበሻ መንገድ አዘጋጅቷል።
አላህ እንዲህ ይላል፥
"ሶላትንም ... ፈጽም። መልካም ሥራዎች ኀጢአቶችን ያስወግድዳሉና።" - ቁርዓን 11፡114
መልዕክተኛው (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ለሶሃቦቻቸው እንዲህ በማለት ውብ ምሳሌ ሰጡ፦ “ከእናንተ አንዳችሁ በቀን አምስት ጊዜ የሚታጠብበት በበሩ የሚያልፍ ወንዝ ቢኖረው፥ ገላው ላይ ቅንጣት እድፍ ሊቀር ይችላልን?”
እነርሱ “አይ።” ሲሉ መለሱ።
ነቢዩም፡ እንዲህ በማለት አከሉ፥ "በተመሳሳይ አላህ በአምስቱ ዕለታዊ ሰላቶች ወንጀሎችን ያብሳል።”
ችግሮችዎን ይፈታል
ከአላህ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ካጠናክሩ፥ አላህ ደግሞ ከተቀረው ፍጥረተ አለም ጋር ያለዎትን ግንኙነት ያጠናክርሎታል።
በሰላት አማካይነት፥ እርሱ፥ እጅግ ኃያል የሆነው፥ ሁሉንም ችግሮችዎን ያስተካክላቸዋል።
አላህ እንዲህ ይላል፥
"በመታገስና በሶላት ተረዱ፡፡" - ቁርዓን 2፡153
ሙስሊሞችን አንድ ያደርጋል
የጋራ (የጀምዓ) ሰላት በሙስሊሞች መካከል ወንድማማችነትን፣ እኩልነትንና መተናነስን ይኮተኩታል።
ሰጋጆች እንደ አንድ አካል፥ ያለምንም የዘር፣ የዜግነት፣ የቆዳ ቀለም፣ የሐብት፣ የቤተሰብ ወይም የማህበራዊ ደረጃ ልዩነት ትከሻ ለትከሻ ገጥመው በረድፍ ይቆማሉ።
ይህ የአንድነት ተግባር በሰዎች መካከል የሚቆምን ማንኛውም ግድግዳ ያፈራርሳል።
ሰላትን መተው
"አንተ ሰው ሆይ! በቸሩ ጌታህ ምን አታለለህ?" - ቁርዓን 82፡6
የፈጣሪዎን ትዕዛዝ እየጣሱ ነው
የመኖርዎ ሙሉው ዓላማ አላህ ማምለክ ሆኖ ሳለ፥ ሆኖም ግን በየዕለቱ፥ የፈጣሪዎን ትዕዛዝ በመጣስ ላይ ነዎት።
"ከእነሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተዉ) ፍላጎቶችንም የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ። ግን የተጸጸተና ያመነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ። አንዳችንም አይበደሉም።" - ቁርዓን 19፡59-60
"(ይሏቸዋልም) ‘በሰቀር ውስጥ ምን አገባችሁ?’ (እነርሱም) ይላሉ ‘ከሰጋጆቹ አልነበርንም። ...’" - ቁርዓን 74፡42-43
ምስጋና ቢስ እየሆኑ ነው
ከፈጣሪዎ ያለዎትን ቅርብ ግንኙነት ለመመስረት ያደረጋቸውን ዕዳምና ትእዛዝ ማቋረጥ ምርጥ መጥፎነት ነው።
ሰላትን መተው (የቀጠለ)
አላህ ፈጥሮዎ ሲያበቃ ሁሉን ነገር ሰጥቶዎታል።
"’እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም መስሚያና ማያዎችን፣ ልቦችንም ያደረገላችሁ ነው። ጥቂትንም አታመስግኑም’ በላቸው።" - ቁርዓን 67፡23
ለረጅም ሰዓታት ሰላት ላይ ከመቆም ብዛት የነብዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እግሮች እስከ ማበጥ ይደርሱ ነበር።
ስለዚህ በተጠየቁ ጊዜ፥ እንዲህ ብለው መለሱ፥ "ለጌታዬ አመስጋኝ ባሪያ ልሆን አይገባምን?"
ሰነፍ እየሆኑ ነው
በመጨረሻው የፍርድ ቀን ሰማይንና ምድርን ለፈጠረው ፈጣሪዎ ምን ሰበብ ያቀርባሉ?
ያ 24 ሰዓታት ባሉት ቀን የባረከዎ፥ ግን በቀን አምስት ጊዜ ብቻ እንዲሰግዱ የጠየቀዎት።
ነቢዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥ "የአደም ልጅ በትንሳኤ ቀን እነዚህን አምስት ነገሮች ሳይጠየቅ ከጌታው ፊት ዘወር እንዲል አይደረግም፥ ህይወቱን እና እንዴት እንዳሰለፋት፣ ወጣትነቱን እና እንዴት እንደተጠቀመበት፣ ገንዘቡን እና እንዴት እንደከሰበውና ምን ምን እንዳደረገበት፣ ያገኘውን እውቀት እና እንዴት ተግባር ላይ እንዳዋለው።”
ነጭናጫ ይሆናሉ
አላህ እንዲህ ይላል፥
"ከግሣጼዬም የዞረ ሰው ለእርሱ ጠባብ ኑሮ አለው። በትንሣኤም ቀን ዕውር ሆኖ እንቀሰቅሰዋለን።
‘ጌታዬ ሆይ! ለምን ዕውር አድርገህ አስነሳኸኝ በእርግጥ የማይ የነበርኩ ስሆን?’ ይላል።
(ነገሩ) እንደዚሁ ነው። ‘ታምራታችን መጣችልህ። ተውካትም። እንደዚሁም ዛሬ ትተዋለህ’ ይለዋል።" - ቁርዓን 20፡124-126
ራስዎን ብቻ እየጎዱ ነው
አላህ ሰላትዎንም ሆነ ከማንም ምንንም ነገር ፈላጊ አይደለም - ጥራት የተገባው ይሁን! እዝነቱን ፈልገው ከፊቱ የሚቆሙት እርስዎ ነዎት።
"አላህን አመስግን። ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው ለራሱ ብቻ ነው። የካደም ሰው (በራሱ ላይ ነው)። አላህ ተብቃቂ ምስጉን ነውና።" - ቁርዓን 31፡12
ከክህደት (ኩፍር) ጋር እየተጎነታተሉ ነው
ብዙ የእስልምና ምሁራን፥ የሚከተለውን ሐዲስ በመጥቀስ፥ ‘ሶላት የማይሰግዱ ከሆነ ካሃዲ ነዎት’ የሚል አቋም ነው ያላቸው።
“እኛን ከእነሱ (ማለትም፥ አማኞችና ከካሃዲያን) የሚለየን ቃል ኪዳን (ድንበር) ሶላትን መተው ነው። (ሶላትን) የተወ በእርግጥ ካደ።”
ከዚህም በተጨማሪ፥ የነቢዩ ሶሃቦች (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) ከሶላት በስተቀር ሌላን ማንኛውም አይነት የአምልኮ ተግባር መተውን እንደ ክህደት አልተመለከቱም።
የተለመዱ ሰበቦች
የጊዜ አለመኖር (ሥራ፣ ትምህርት፣ ቢዚ መሆን፣ ወዘተ.): ጥርት ያለ ቀላል ማታለያ። ለሶላቶችዎ ቅድሚያ አልሰጡም። አላህ ጊዜዎት ላይ በረካን ያደርግሎታል ብሎም ይበልጥ ውጤታማ፣ ትርፋማ እና ስኬታማ ያደርጎታል።
ልቤ ንጹህ ነው፥ ማን ንፁህ ልብ እንዳለው አላህ ነው ፈራጁ፥ ፍላጎቱ እርስዎ እንዲሰግዱ ነው! ተግባራት ልቦዎ ውስጥ ምን እንዳለ ያንፀባርቃሉ። በመደበኛነት ሰላት ይሰግዱ ከነበሩት ነቢዩ ሙሃመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ይበልጥ የነፃ ልብ ያለው ማንም የለም።
አላርሜ፥ አላርምዎን በትክክል ካልሞሉት ሊጮህ አይችልም!! ኒያዎትን ንፁህ ያድርጉና በሱናው መሰረት ይተኙ።
ቤተሰቤ/ባለቤቴ/ወላጆቼ/ወዳጆቼ ይከለክሉኛል፥ ነብዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) እንዲህ ብለዋል፥ "የአላህን ትዕዛዝ በመጣስ ለማንም ታዛዥ መሆን የለም።” ለፍርድ የሚቀርቡት ብቻዎትን ነው።
አብዝቼ ኃጢአት እስራለሁ፥ በጊዜ ሂደት ሶላቶችዎ እነዚህን ኃጢአቶች ከመፈፀም ያግዱዎታል - ዝም ብለው ይስገዱ! ኃጢአት የሚሰሩት ባለመስገድዎ ነው።
ይህን ሐዲስ ያጢኑት፥ “የኢሻዕ እና የሱብሂ ሰላቶችን ጥቅሞች ቢያውቁ ኖሮ እየዳሁም ቢሆን (ወደ መስጊድ) ይመጡ ነበር።”
በዚያ አስቸጋሪ (የትንሳኤ) ቀን ከጌታዎ ፊት ሲቀርቡ፥ ሰላት ለመተወዎ ምን እውነተኛ ሰበብ ይኖርዎታል?
