ስለ እስልምና የተሳሳቱ እይታዎች

2.32 MB 139 1 Files
albyan
or download free
[free_download_btn]

Description

የምር ግን ስለ እስልምና ምን ምን ያውቃሉ?

መግቢያ

እስልምና ክዓለማችን ታላላቅ ሃይማኖቶች ውስጥ አንዱ ሆኖ ሳለ፥ ለተዛቡ እይታዎች በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ ከሆኑትም ውስጥ ተጠቃሽ ነው።

በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ - ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ኢሚዛናዊ የሚዲያ አቀራረብም ይባል “ሌላው”ን በጭፍን የመፍራት አባዜ - ስለ እስልምና ከሐቅ የራቁና የተሳሳቱ እይታዎች ሲሰራጩ ቆይተዋል።

እስልምናን እና ሙስሊሞችን ለመረዳት ቁልፉ መንገድ ለአጉል ፍረጃዎች ቦታ አለመስጠት እና እያንዳንዱን ሁኔታ ከኢስላማዊ አስተምህሮቶችና ከታማኝ ምንጮች አንፃር መመርመር ነው።

የተሳሳተ እይታ 1 - "ሙስሊሞች ሙስሊም ካልሆኑ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር መልካም እና ክቡር እሴቶችን አይጋሩም"

"ከእናንተ ውስጥ በላጮቹ ምርጥ ስነምግባርና ባህርይ ያላቸው ናቸው።" - ነቢዩ ሙሃመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን)

ኢስላማዊ እሴቶች ጨዋ ከሚባሉ “ምዕራባዊ” እሴቶች ጋር እምብዛም እንደማይጣጣሙ አንዳንድ ሰዎች አቤቱታ ያቀርባሉ። መሰል አቤቱታዎች ከእውነታው የራቁ ሊሆኑ አይችሉም።

ሙስሊሞች እንደሚከተሉት ለመሳሰሉ ክቡርና አለም አቀፋዊ እሴቶች ከፍተኛ ዋጋ ይሰጣሉ፦

• ታማኝና ፍትሐዊ መሆን

• ቃልን መጠበቅ

• የሃይማኖት ነጻነትን መፍቀድ

• ወላጆችን፣ ዘመድ አዝማድን፣ ጎረቤቶችን፣ እና አረጋዊያንን ማክበር

• ቸርነት፣ ለጋስነት እና ለድሆችና ለችግርተኞች ማዘን

• ለጎረቤት እንክብካቤ ማድረግ

• አለመዋሸት፣ አለማታለል፣ አለመራገም አልያም ማንንም አለማማት

ሙስሊሞች ለማኅበረሰብ አዎንታዊ አስተዋፅዖ እንዲኖራቸው እና ሁሌም በከፍተኛ ስነምግባራዊ ልዕልና እና በምርጥ ተግባራት ህይዎታቸውን እንዲመሩ ይጠበቅባቸዋል።

የተሳሳተ እይታ 2 – "ሙስሊሞች አላህ ተብሎ የሚጠራን አዲስ አምላክ ያመልካሉ"

ሙስሊሞች በእነ ነብዩ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ሙሴ እና ኢየሱስ የተመለከውን ያንኑ ተመሳሳይ አምላክ ያመልካሉ።

"አላህ" በቀላሉ ሁሉን ቻይ የሆነውን ሐያል አምላክ የሚወክል አረቢኛ ቃል ነው። በአረቢኛ ቋንቋ አንዱንና ብቸኛውን አምላክ የሚያመለክት ጥልቅ ፍቺን ያዘለ ቃል ነው።

በተጨማሪም አላህ አረቢኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖችና ይሁዲዎች አምላክን ለማመልከት የሚጠቀሙት ተመሳሳይ ቃል ነው።

ይሁን እንጂ፥ ሙስሊሞች፣ ይሁዲዎችና ክርስቲያኖች በአንድ አይነት አምላክ (ፈጣሪ) የሚያምኑ ቢሆኑም፥ እሱን በተመለከተ ያሏቸው ፅንሰ ሃሳባዊ አተያዮች በከባዱ ይለያያሉ።

ለምሳሌ፥ ሙስሊሞች የአምላክን አጋር ያለው አልያም የ”ስላሴ” አንድ አካል የመሆን ሃሳብ አይቀበሉም፤ ብሎም ፍፁምነትን ሁሉን ቻይ ለሆነው ሐያል አምላክ ብቻ ይሰጣሉ።

የተሳሳተ እይታ 3 – "እስልምና ሽብርተኝነትን ይፈቅዳል"

የዜና አውታሮች በአጠቃላይ ማንኛውንም ተዋጊ ሙስሊም ሽብርተኛ አድርገው ይስላሉ፤ የሚዋጉት ለፍትህና ለነፃነት ይሁን አይሁን፥ ሌሎች ላይ ጭቆናን እየፈፀሙ ይሁን ወይስ ራሳቸው ተጨቁነው ግምት ውስጥ አይገባም።

በጦርነት ወቅት፥ ውጊያ ላይ የማይሳተፉ ንፁሃን ዜጎችን ኢላማ ማድረግ እስልምና በግልፅ የሚከለክለው የሚናቅ ተግባር ነው።

እንዲያውም፥ ሙስሊሞች ንፁሃን የሰው ልጆችን ይቅርና ዕፅዋትንና እንስሳትን እንኳ ያለምክንያት እንዲያወድሙ አልተፈቀደላቸውም።

ሆኖም ግን፥ ሽብርተኝነትን ህጋዊ ከሆነ ወረራን የመቃወም ተጋድሎ ለይቶ መመልከት አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም ሁለቱ በጣም የሚለያዩ ጉዳዮች ስለሆኑ።

ቅዱስ ቁርዓን የንፁህ ግለሰብን ነፍስ የመቅጠፍን አደገኛነት በግልፅ ያብራራል፤ ብሎም የሰው ነፍስን ክቡርነት በአንክሮ እና የሰውነትን እንደ እሴት አመለካከቱን እንደሆነ ያሳያል።

“ንፁህ የሆነችን ነፍስ የገደለ ሰው መላው የሰው ዘርን እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው መላው የሰው ዘርን ሕያው እንዳደረገ ነው" ቁርዓን 5፡32

የተሳሳተ እይታ 4 – "እስልምና ሴቶችን ይጨቁናል"

በእስልምና ውስጥ፥ ወንዶችና ሴቶች በአላህ ፊት በእኩል አይን ይታያሉ - ምንዳዎችን ከመመንዳትም ሆነ ለሚፈፅሟቸው ወንጀሎች ከሚኖራቸው ተጠያቂነት እኩልነት አንፃር።

ሰዎችን በአላህ ፊት የሚያበላልጣቸው ብቸኛ ነገር ያላቸው የቅድስና (ሐይማኖተኛነት) ደረጃ ነው።

“አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው።” ቁርዓን 49፡13

አንድ ሰው እውነተኛ ክብርንና ደረጃን የሚጎናፀፈው ሐብታም ወይም ድሃ፣ ጥቁር ወይም ነጭ፣ ወንድ ወይም ሴት በመሆኑ ምክንያት ሳይሆን በአሏህ ፍራቻውና በመንፈሳዊ ትጋቱ አማካይነት መሆኑን ይህ የቁርዓን አንቀፅ ያረጋግጣል።

አላህ፥ የሁለቱም ጾታዎች ፈጣሪ፥ ልዩነቶቻቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለእያንዳንዳቸው የተለያዩ ሚናዎችን እና ሐላፊነቶችን ሰይሞላቸዋል።

ሴቶች ከፍተኛ አክብሮትና ፀጋ ተችሯቸዋል፤ ለምሳሌ ያህል የእኩል ተከፋይነት፣ የትዳር አጋርን የመምረጥ፣ የመማር፣ የፍች እና የውርስ መብቶች አሏቸው።

እንዳለመታደል ሆኖ በጭቆና ውስጥ የሚኖሩና መብቶቻቸውን የተነፈጉ አንዳንድ ሙስሊም ሴቶች አይታጡም።

ይህ የእስልምና ጥፋት አይደለም።

ችግሩ ያለው በአንዳንድ ሃገራት ሰዎች ከእስልምና ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌላቸውን የተወሰኑ ባህላዊ የአኗኗር ዘይቤዎችን እና ልማዶችን የሚከተሉ መሆናቸው ላይ ነው።

የተሳሳተ እይታ 5 – "ቅዱስ ቁርዓን በቃ ሌላ የታሪክ አልያም የስነ ግጥም መፅሐፍ ነው"

ቅዱስ ቁርዓን በመላዕኩ ጂብሪል በኩል ለነቢዩ ሙሀመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) የተገለፀላቸው የሐያሉ አምላክ ቀጥተኛ መለኮታዊ ቃል ነው።

የሐቅ አንደኛው መስፈርት ሲሆን፥ የሰው ልጆች ሕይወታቸውን ይመሩበት ዘንድ በውስጡ መመሪያን ይዟል።

ቅዱስ ቁርዓን፥ ከተሞክሮዎቻቸው እንማር ዘንድ የቀደምት ትውልድ አስተምህሮዎችን እና የነቢያትን ታሪክ ይጠቅሳል።

ከዚህም ባሻገር ስለራሳችን እና ስለፈጣሪያችን እንዲሁም ስለተፈጠርንበት አላማ፥ ይኸውም አሏህን አውቀን እሱን ብቻ እንድንገዛ መሆኑን፥ ያስተምረናል።

አላህ የሰው ልጆችን ያለ አላማ ዝም ብለው እንዲያውደለድሉ አይደለም የፈጠራቸው።

የአንድ ሰው እምነት የሚለካው የአሏህን ምልክቶች በማስተንተን ለይቶ ለማስተዋል አእምሮውን፣ ነፃ ምርጫውን እና አመክንዮውን በመጠቀም ብቃቱ ነው። ቁርዓን ደግሞ እጅግ ከላቁት ምልክቶች ውስጥ አንዱ ነው።

ቅዱስ ቁርዓን፥ ስለትክክለኛነቱ ምንም አይነት ጥርጣሬ እንዳይገባን የሚያስችሉ በርካታ ተዓምራትን በውስጡ ይዟል።

ቅዱስ ቁርዓን በተጨባጭ ስለ ምን እንደሆነ ለማወቅ እጅግ ተመራጩ ዘዴ በራስዎ መፅሃፉን ማንበብ ነው።

የተሳሳተ እይታ 6 – "ሂጃብ ማድረግ መጨቆን ነው"

ሂጃብን ለመጠበቅ፥ ሙስሊም ሴቶች የቅርብ ዝምድና በሌላቸው ወንዶች ፊት የሰውነት ቅርፃቸውን በማያጋልጡ አልባሳት አካላቸውን መሸፈን ግድ ይላቸዋል።

ነገር ግን፥ ሂጃብ ስለውጫዊ ገፅታዎች ብቻ የሚመለከት ጉዳይ አይደለም፤ ስለ መልካም ንግግር፣ ስለ ጨዋነት እና በአክብሮት ስለተሞላ ጠባይም ጭምር እንጂ።

ምንም እንኳ ሂጃብ በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት ቢሆንም፥ ሙስሊም ሴቶች ሂጃብን የሚጠብቁበት ቁልፉ ምክንያት ከአላህ የመጣ ትእዛዝ ስለሆነ ነው፤ ደግሞም እርሱ ለፈጠረው አካል የሚበጀውን ነገር አዋቂ ነው።

ሂጃብ ከውጫዊ አቋሟ ይልቅ የውስጥ መንፈሳዊ ውበቷን በማጉላት ሴትን ልጅ ኃይል ይሰጣታል።

ክብራቸው እንደተጠበቀ፥ ንቁ የማህበረሰብ አባላት የመሆን ነፃነትን ለሴቶች ይሰጣል።

ሂጃብ አፈናን፣ ጭቆናን አልያም ዝምታን አይወክልም።

ይልቁንም፥ ክብርን ከሚያሳንሱ ለከፋዎች፣ ካላስፈላጊ ጉንተላዎች እና ከኢፍትሐዊ መድልዎ መጠበቂያ ጋሻ ነው።

ስለዚህ በቀጣይ ጊዜ አንዲትን ሙስሊም ሴት ሲያዩ፥ የሸፈነችው ውጫዊ አካሏን እንጂ አእምሮዋን አልያም አስተሳሰቧን አለመሆኑን ይወቁ።

የተሳሳተ እይታ 7 – "ሁሉም ሙስሊሞች አረቦች ናቸው"

በዓለም ላይ ካሉ ሙስሊሞች 20% የሚሆኑት ብቻ ናቸው አረቦች፤ ይህም ማለት እስከ 80% የሚደርሰው ሙስሊም አረብ አይደለም ማለት ነው።

ለምሳሌ፥ ከአረብ ሙስሊሞች የሚበልጡ የህንድና የኢንዶኔዥያ ሙስሊሞች አሉ።

በዘሩ አልያም በቆዳው ቀለም ምክንያት አንድ ግለሰብ ከሌላው እንደማይበልጥ እስልምና ያስተምራል፤ እናም የትኛውንም አይነት ዘረኝነት በጥብቅ ይቃወማል።

እስልምና ለሰው ዘር በመላ የሚሆን መልዕክት አለው፤ ይኸውም፥ ሁሉም ሰው አንድዬውን እውነተኛ አምላክ አምኖ በመቀበል እና በማምለክ ብቻ ሰላምና ስኬትን ሊቀዳጅ ይችላል የሚል ነው።

የተሳሳተ እይታ 8 – "ጂሃድ ሽብርተኝነት ነው"

የጂሃድ መሰረታዊ ነገር አምላክን በሚያስደስት መልኩ ለሐይማኖት ተጋድሎ ማድረግ እና መስዋዕትነት መክፈል ነው።

ከስነልሳን አንፃር "ተጋድሎ" ማድረግ ማለት ሲሆን አንድ ሰው መልካም ስራዎችን ለመስራት፣ በጎ አድራጎትን ለመፈፀም አልያም ኢስላማዊ ውትድርናን ለመቀላቀል የሚያደርገውን ጥረት ሊያመለክት ይችላል።

በጣም በስፋት የሚታወቀው፥ የማህበረሰብን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ የጭቆና መንሰራፋትን ለመግታት እና ፍትህን ለማረጋገጥ የሚፈቀደው ወታደራዊው የጂሃድ አይነት ነው።

ይህም እንደየሁኔታው መከላከል አልያም ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል።

የተሳሳተ እይታ 9 – "ሙስሊሞች ሙሀመድን ወይም የጨረቃን አምላክ ያመልካሉ"

ሌላኛው የተሳሳተ እይታ ሙስሊሞች ነቢዩ ሙሀመድን (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ያመልካሉ የሚለው ነው። ይህ ሙሉ በሙሉ ውሸት ሲሆን “ክርስቲያኖች የማርያምን ልጅ ኢየሱስን አብዝተው እንዳሞገሱት እኔንም አብዝታችሁ አታሞጋግሱኝ። እኔ የእርሱ ባሪያ ነኝ፤ በመሆኑም ‘የአሏህ ባሪያ እና መልዕክተኛ’ ብላችሁ ጥሩኝ” በሚለው የነብዩ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ተጨባጭ ቃል በቀላሉ የሚስተባበል ነው።

እስልምና ሁሉንም የአላህ ነቢያትና መልዕክተኞች እንዲያከብሩ ሙስሊሞችን ያስተምራል፤ ነገር ግን እነርሱን ማክበርና መውደድ ማምለክ ማለት አይደለም።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳ ወቀሳ ሙስሊሞች “የጨረቃ አምላክ” ያመልካሉ የሚል ነው፤ ፈፅሞ ትክክል አይደለም። ጨረቃንም ሆነ ከአላህ ውጪ የሆነን ሌላ ማንኛውም ነገር ማምለክ በእስልምና ሐይማኖት በጥብቅ የተከለከለ ነው።

"ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ። ለእዚያም ለፈጠራቸው አላህ ስገዱ። እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደሆናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)።" ቁርዓን 41፡37

እስልምና የአላህን ምሉዕነት፣ ሐያልነት እና ብጤ የለሽነት ያለ አንዳች መቀናነስ አምኖ ይቀበላል። እርሱ እጅግ ፍትሐዊ፣ እጅግ መሐሪ ነው።

እርሱን ብቻ መገዛት በእስልምና እጅግ ወሳኙ እምነት ነው - በቅዱስ ቁርዓን ብዙ ቦታዎች ላይ እንደተገለፀው።

የተሳሳተ እይታ 10 – "እስልምና ግዳጅ ጋብቻዎችን ይፈቅዳል"

ልጅህን ለልጄ የመሰጣጠት ጋብቻዎች በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የተወሰኑ አገራት በስፋት የሚፈፀሙ ባህላዊ ልማዶች ናቸው።

ምንም እንኳ ልማዱ የሙስሊሞች ብቻ ባይሆንም፥ ግዳጅ ጋብቻ በተሳሳተ መንገድ ከእስልምና ጋር ተያይዞ ይነሳል።

በእስልምና፥ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ውሃ አጣጭ ሊሆኗቸው የሚችሉ ሰዎችን የመምረጥ ወይም አልፈልግም የማለት መብት አላቸው፤

እናም ከጋብቻው ቀደም ብሎ እንስቲቱ እውነተኛ ፈቃደኝነቷን ያልሰጠችበት ጋብቻ ዋጋ የሌለውና ውድቅ ተደርጎ ነው የሚወሰደው።

የተሳሳተ እይታ 11 – "እስልምና ሰዎችን ሙስሊም እንዲሆኑ በጉልበት ያስገድዳል"

አላህ እንዲህ ይላል፥ “በሃይማኖት ማስገደድ የለም። ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ።” ቁርዓን 2፡256

የእስልምናን ውብ መልእክት ለሌሎች ማድረስ እና ማጋራት የሙስሊሞች ግዴታ ቢሆንም፥ ማንም ሰው እስልምናን እንዲቀበል ሊገደድ አይችልም።

እስልምናን ለመቀበል፥ አንድ ሰው በሙሉ ልቡ እና በፈቃደኝነት ፈጣሪን ማመንና መታዘዝ አለበት። ስለዚህ በመሰረቱ ማንም ሰው እስልምናን እንዲቀበል ሊገደድ አይችልም (ወይም መገደድ የለበትም)።

ቀጣዮቹን ነጥቦች ያጢኑ፦

• ኢንዶኔዥያ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሙስሊም ህዝብ አላት፤ ሆኖም ግን እስልምናን እዚያ ለማስገባት አንድም ጦርነት አልተካሄደም።

• ወደ 14 ሚሊዮን የሚጠጉ አረብ የሆኑ ቅብጣዊ ክርስቲያኖች አሉ፥ በአረቢያ ምድር እምብርት ለዘመናት የኖሩ።

• እስልምና ዛሬ ላይ በምዕራቡ ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ካሉ ሃይማኖቶች መካከል አንዱ ነው።

• ጭቆናን መታገል እና ፍትህን ማስፋፋት ጂሃድን ለማወጅ ቅቡል ምክንያቶች ቢሆኑም፥ ሰዎች እስልምናን እንዲቀበሉ በሃይል ማስገደድ ግን ከምክንያቶቹ አንዱ አይደለም።

• ሙስሊሞች ለ800 ዓመታት ያህል ስፔንን አስተዳድረዋል፤ ነገር ግን ሰዎች ሃይማኖት እንዲለውጡ እጅ ጠምዝዘው አያውቁም።

ማጠቃለያ

ተዓማኒነታቸውን ሳያረጋግጡ ብቁ ካልሆኑ ምንጮች ስለእስልምና መማር አደገኛ እና ወደተዛባ ግንዛቤ ይመራል።

ስለእስልምና፥ ከሩቡ በላይ የሚሆነው የሰው ዘር ስለሚጋራው እምነት፥ የተንሻፈፉ እይታዎችን እና ሐሰተኛ መረጃን ተሳስተው ወደመቀበል አይወሰዱ።

Similar Downloads

No related download found!