Description
የእስልምና ጥቅሞች
ተግባራዊና ሚዛናዊ የሕይወት መንገድ
ከአላህ ጋር ቅርብና ቀጥተኛ ግንኙነት
ንፁህና ግልጽ የአላህ ግንዛቤ
አለም አቀፋዊና ጊዜ የማይሽረው መልእክት
መሠረታዊያኑን ይወቁ
እስልምና ምንድን ነው?
እስልምና ማለት በብቸኛው እውነተኛ አምላክ (በአረቢኛ “አላህ”) ማመን እና እሱን ብቻ መገዛት፤ እንዲሁም ነቢዩ ሙሐመድን (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) የመጨረሻ መልእክተኛው አድርጎ መቀበል ማለት ነው።
ቢያንስ ከ4 ሰዎች አንዱ (23%) ሙስሊም ነው - ከ1.5 ቢሊዮን በላይ ሙስሊሞች አሉ።
የእስልምና ተከታዮች ሙስሊሞች በመባል የሚታወቁ ሲሆን ከየትኛውም ዘር ወይም ብሔር የመጡ ሊሆኑ ይችላሉ።
እምነት እና አመለካከት
አላህ በምልክቶቹ አማካይነት እወቁኝ እያለ ወደኛ ይጣራል። አላህ እሱን ለይተን ማወቅን የኛ ሃላፊነት አድርጎታል። ይህም የዚህ አለም ህይወት ፈተና አካል ነው። ትክክለኛ አመለካከት ሳይኖር፥ የፈለገውን ያህን የመረጃ ጋጋታ አንድን ሰው እንዲያምን ሊያደርገው አይችልም።
ተጨባጭነት እና ትሁት ክፍት ልቡና
ትህትና እና ቀናዒነት
ስለተፈጠርንበት አላማ ማውጠንጠን
የአላህ ምልክቶችን ተቀባይነት
ያለማመን መሰረት የሌለው ጭፍን ምርጫ
ኩራት እና ትዕቢት
ቁሳዊ አለም ላይ ብቻ ማተኮር
ሁሉንም ነገር ትርጉም የለሽ አድርጎ ወዲያ ማለት
ምክንያት 1
የአፅናፈ አለሙ አጀማመር
በአላህ ለማመን የመጀመሪያው ምክንያት በአፅናፈ አለሙ ምንጭ ዙሪያ ፅብረቃ ከማድረግ ጋር የሚያያዝ ነው።
አፅናፈ አለሙ እንዴት ነው የተገኘው?
ከምንም ነገር ነው የተከሰተው?
ከምንም ነገር፥ ምንም አይገኝም። ስለዚህ ከምንም እንዳልተገኘ ግልጽ ነው።
ራሱን በራሱ ፈጥሮስ ይሆን?
የለም፥ ይህ መሰረተ ቢስ ነው። አንዲት እናት ራሷን ወለደች እንደማለት ነው የሚመስለው።
ሁልጊዜም ነበርን?
አይደለም። አፅናፈ አለሙ ዘላለማዊ አለመሆኑን እና መነሻም እንደነበረው ዘመናዊ ሳይንስ ያረጋግጣል።
ተፈጥሮስ እንደሆነ?
አዎ። ሙስሊሞች ከአፅናፈ አለሙ የላቀ ነገር - ፈጣሪ - እንዳስገኘው ያምናሉ።
ጥያቄ፦ ነገር ግን አላህን ማን ፈጠረው?
መልስ፦ አላህ አልተፈጠረም። ከአፅናፈ አለሙ እና ከቀሪው ፍጥረተ አለም በተለየ፥ አላህ ዘላለማዊ ነው፤ ሁልጊዜም ነበር፤ እንዲሁም መጀመሪያ የለውም።
ምክንያት 2፡ የአፅናፈ ዓለሙ ሥርዓት
በአላህ ለማመን ሌላ ቀላል ምክንያት የሚከተለውን ሎጂክ በመጠቀም ስለአፅናፈ አለሙ ስርዓት ማሰብ ነው፦
1. ስርዓት ያለው ማንኛውም ነገር ምጥቀትን ያሳያል።
2. ሶላር ሲስተማችን ከተራቀቁ ኡደቶች፣ ህግጋትና ውቅሮች ጋር በከፍተኛ ደረጃ ስርዓዊ ነው።
3. በአፅናፈ አለማችን ውስጥ ያለው ሥርዓት የፈጣሪን ምጡቅነት ያሳያል!
በአፅናፈ አለሙ ውስጥ ያሉ በርካታ ገፅታዎች ሕይወትን እንዲያግዝ ተደርጎ በልዩ ሁኔታ የተበጀ መሆኑን በግልጽ ያመለክታሉ።
እነዚህ መጠንታት አሁን እንደሆኑት ቢለዋወጡ ሕይወት ሊኖር አይችልም።
ከታች ምሳሌዎች።
የኦዞን ሽፋን
የመሬት ውጫዊ ክፍል ውፍረት
በአየር ውስጥ የሚገኘው የኦክስጅን ፐርሰንቴጅ
ከፀሐይ ያለን ርቀት
የፀሐይ፣ የመሬት እና የጨረቃ አንፃራዊ መጠን
አንድ ግዙፍና ውስብስብ የሆነ አፅናፈ አለም፥ ያለ ክትትል፥ በአጋጣሚ ሊከሰት ይችላልን?
እስልምና ሳይንሳዊ ምርምርን እና ፅብረቃን እንደሚያበረታታ ማስታወስ ይገባል።
የሳይንስ ሚና አላህ በፍጥረተ አለሙ ያስቀመጣቸውን በርካታ የሚታዩ ቀመሮች ለመግለፅ እና የሐያልነቱንና ጥበበኛነቱን መጠን ለማድነቅ ይረዳናል።
ምክንያት 3
መለኮታዊ መገለጥ – ቁርዓን
ቅዱስ ቁርዓን ፈጣሪ ለመኖሩ ጠንካራ ማሳመኛዎችን ያቀርባል፤ እናም በቋንቋ ስልቱ፣ በጥበቡ፣ በምክሮቹ፣ በርቱዕነቱ እንዲሁም አንባቢን በሚጠራበት የተለየ አቀራረቡ አቻ አይገኝለትም።
ግድፈቶችም ሆነ መጣረሶች የሉበትም።
ንጹሕና ግልጽ የአላህ ገለፃዎች
የአረቢኛ ስነልሳናዊ ውበት ከፍታ
መሐይም በነበሩት በነቢዩ ሙሐመድ (ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) በኩል የተገለጠ
ተጠብቆ የኖረና በ1400 ዓመታት ውስጥ ምንም ያልተለወጠ
ስለሰው ልጅ ጠባይ ጥልቅ እይታዎች
በሚልዮኖች በቃል የተጠና
በዚያን ዘመን የማይታውረቁ ሳይንሳዊ እውነታዎች ይዟል።
“በምድርም ውስጥ ለሚያረጋግጡ ሰዎች ምልክቶች አልሉ። በነፍሶቻችሁም ውስጥ (ምልክቶች አልሉ)፤ ታዲያ አትመለከቱምን?” (ቅዱስ ቁርዓን 51:20-21)
አላህ ማን ነው?
ከእስልምና ዋነኛ ውበቶች ውስጥ አንዱ የአላህን ምሉዕነት፣ ሐያልነት እና ብጤ የለሽነት ያለ አንዳች መቀናነስ እውቅና መስጠቱ ነው።
· አላህ አንድና ብቸኛ ሲሆን፥ ተቀናቃኞች፣ አጋሮችም ሆኑ ልጆች የሉትም።
· አላህ ሁሉም አምልኮ የተገባው ነው - በቀጥታና በብቸኛነት (ያለአማላጆች)።
· አላህ ፍጹምና እንከን የለሽ ነው - ውስንነቶችም ሆኑ ድክመቶች የሉበትም።
· አላህ እጅግ በጣም ሩህሩህ ነው - እኛ ምሉዕ አለመሆናችንንና ሐጢዓት እንደምንሰራ ያውቃል፤ ቁልፉ ጉዳይ ግን ሁልጊዜም ስህተታችንን አምነን መቀበልና ከልባችን ምህረትን መጠየቅ ነው።
· አንድም የአላህ ክፋይ በፍጡራኑ ላይ አይገኝም፤ መለኮታዊ ስሞቹንም ሌሎች አይጋሯቸውም።
በእስልምና ውስጥ የአላህን ፅንሰ ሐሳብ ለመረዳት በሚሞከር ጊዜ፥ ኢየሱስ ስላለው ደረጃ ማብራራት አስፈላጊ ነው - በስፋት የሚስተዋለውን መደነጋገር እና ስለሱ ተፈጥሮ የሚነሱትን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ በማስገባት።
ኢየሱስ የተከበሩ የአላህ ነብይ እና መልዕክተኛ መሆናቸውን እስልምና አምኖ ይቀበላል፤ ነገር ግን ሙስሊሞች እሳቸውን አያመልኩም - ምክንያቱም አምልኮ የሚገባው ኢየሱስንም ሆነ ሌላውን ነገር ሁሉ ለፈጠረው አንድዬ አምላክ ብቻ ነውና።
ያም ሆነ ይህ፥ ኢየሱስን እንደአምላክ አልያም እንደአምላክ ልጅ ወይም እንደስላሴ አካል አድርጎ መውሰድ፥ እስልምና ስለአምላክ ካለው ንፁህ አስተምህሮት ጋር በግልጽ ይጋጫል።
አምላክ ከእርሱ የተለየ አካል እንደሆነ አድርጎ ኢየሱስ የሚናገርባቸው እና ባህሪውን የሚገልፅባቸው በርካታ ምሳሌዎች በክርስትና አስተምህሮቶች ውስጥ አሉ፤ ለምሳሌ የኢየሱስ ለአምላክ መፀለይ።
ኢየሱስ አምላክ ከነበረ፥ ለማን ሊሆን ይችላል ሲፀልይ የነበረው?
ኢየሱስ ተወልዷል፤ ይበላና ይተኛ ነበር፤ ውስን እውቀትም ነበረው – ሁሉም አምላክን የማይመጥኑ ባህሪያት።
አምላክ ያሉት ባህሪያት ፍፁም ሲሆኑ፥ የሰው ግን በተቃራኒው ነው።
አምላክ እንዴት ባንድ ጊዜ ፍጹም እና ጎዶሎ ሊሆን ይችላል?
"የአምላክ ልጅ" የሚለውን አገላለፅ በጥንታዊያኑ የመፅሃፍ ቅዱስ ቋንቋዎች - ለኢየሱስ ለብቻው ሳይሆን - ለብዙ “አምላክን ፈሪ” ሐይማኖተኛ ሰዎች በተምሳሌታዊ መገለጫነት ጥቅም ላይ ሲውል እናገኛለን።
አምላክ አካላዊም ሆነ ቃላዊ ልጅ ያለው ከመሆን እጅግ የራቀ ነው።
የምር ግን “የአምላክ ልጅ” የሚለው አገላለፅ ምን ማለት ነው?
ጥያቄ፡ አምላክ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እስከቻለ ድረስ፥ ለምን ሰው መሆንስ አይችልም?
አካላዊ እና ቃላዊ ልጅ።
መልስ፡ አምላክ ሁልጊዜም ፍፁም ባህሪያቱ እንደተጠበቁ ሲሆን . . .
የሰው ባህሪያትን ቢላበስ፥ አምላክነቱ የግድ አከተመ ማለት ይሆን ነበር።
ብዙ ነቢያት
ነቢዩ አደም
ነቢዩ ኑህ
ነቢዩ ኢብራሒም
ነቢዩ ሙሳ
ነቢዩ ኢሳ
ነቢዩ ሙሐመድ
ሰላም በሁሉም ላይ ይሁን
1 ተልእኮ
• የአንድ አምላክ ፅንሰ ሐሳብን አበክሮ ማሳሰብ
• ሐሰተኛ አማልክትን እና እምነቶችን ወዲያ መጣል
• አላህ እንዴት እንደሚመለክ ማሳየት
• አርዓያ መሆን
• የአማኝነት ምንዳዎችን (ገነት) መግለፅ
• እምቢተኛነት ስለሚያስከትለው ቅጣት (ገሐነም) ማስጠንቀቅ
አምላክ ለህዝቦች ሁሉ ነቢያትን በመሰረታዊነት ከሚመሳሰል መልእክት ጋር ለዘመናት ሲልክ ኖሯል።
ምንም እንኳ ሙስሊሞች ነብያትን ሁሉ የሚወዱና የሚያከብሩ ቢሆኑም፥ እነርሱን አይመልኳቸውም አልያም የመለኮት ባህሪን ለእነርሱ አይሰጡም፤ ምክንያቱም ይህ ለአምላክ ብቻ የተቀመጠ ነውና።
የሕይወት ዓላማ
እጅግ በጣም ብልሁ አላህ፥ ያለአላማ ዝም ብለን እንድንባዝን አልያም መሰረታዊ የደመነፍስ ስሜቶቻችንንና ፍላጎቶቻችንን ብቻ እንድናሟላ አይደለም የፈጠረን። ይልቁንስ ከፍ ያለ አላማ አለን – በፈጣሪያችን መመሪያ መሰረት እንኖር ዘንድ አላህን ማወቅና እሱን ብቻ መገዛት።
ይህ መምሪያ በሁሉም ረገድ የተረጋጋ እና ስኬታማ ህይወት እንድንኖር ያስችለናል።
እኛን ፈጥሮን ሲያበቃ፥ እሱን እንድናውቀው፣ ህይዎታችንን እንድንኖር እና የምርጫችንን እንድንፈፅም እድል መስጠቱ የአላህ ገደብ የለሽ ጥበብ አካል ነው።
እስልምና፥ ሙስሊሞች ሚዛናዊ፣ ትሁት እና ለማህበረሰብ አስተዋፅዖ ያላቸው አባላት እንዲሆኑ የሚያስተምር ምሉዕ እና ተግባራዊ የህይወት መንገድ ነው።
እስልምና ውስጥ የአምልኮ ፅንሰ ሐሳብ ለአላህ መስገድን እና መፀለይን ብቻ አያጠቃልልም። አላህ የሚደሰትበትን ማንኛውም ተግባር የሚያጠቃልል ሰፊ ብያኔ እንጂ። ምሳሌዎች ቀጥሎ ቀርበዋል።
• በሐቀኛ ገቢ (ርዚቅ) መኖር
• ጭቆናን መቃወም
• ወላጅ አልባ (የቲም) ታዳጊዎችን መንከባከብ
• የአካባቢ እንክብካቤ ማድረግ
• ታጋሽ እና ትሁት መሆን
• ማኅበረሰቡን መጥቀም
• ወላጆችን ማክበር
• ለፍትሕ ዘብ መቆም
• ለጎረቤቶች ደግ መሆን
• አላህን ልብ ማለት
• ቤተሰብን መርዳት
• እውነትን መናገር
የአምልኮ ተግባራት አላህን ለማስደሰት ከልብ ማሰብን የሚፈልጉ ሲሆን በኢስላማዊ መመሪያዎች መሰረት በትክክል መፈፀም ይኖርባቸዋል።
እስልምና ስለ ... ምን ይላል?
• ሴቶች: በእስልምና ውስጥ ሴቶች ከፍተኛ ክብር አላቸው። በፍቅር፣ በሞገስ እና በአክብሮት ሊስተናገዱ ግድ ነው። የወንድ አጋር ሲሆኑ ምንም አይነት ጭቆና በእነሱ ላይ ሊጫን አይገባም።
• ሽብርተኝነት: እስልምና የማኅበረሰብ ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የጭቆና መስፋፋትን ለመከላከል እና ፍትህን ለማረጋገጥ ፍልሚያን ይፈቅዳል። ነገር ግን፥ ፍልሚያ ላይ የማይሳተፉ ንፁሃን ዜጎችን ኢላማ ማድረግ የተከለከለ ውግዝ ተግባር ነው።
• ሀላል ምግብ: ሀላል ምግቦች ሙስሊሞች እንዲበሉ የተፈቀዱላቸው ህጋዊ ምግቦች ናቸው። የሥጋ ከብቶችና ዶሮ ሰብዓዊነትን በተላበስና ስቃይን በሚቀንስ ሁኔታ የአላህ ስም ተጠርቶባቸው ሊታረዱ ይገባል።
• ዝግመተ ለውጥ፡ አላህ የመጀመሪያውን ሰው፥ አደም፥ በመጨረሻ ቅርፁ ፈጥሮታል - ከሰለጠኑ ጦጣዎች ቀስ በቀስ በዝግመተ ለውጥ እንደተገኘ ከሚነገረው በተቃራኒ። ሳይንስ ይህን በቀጥታ ሊያረጋግጥ አልያም ሊክድ አይቻለውም፤ ምክንያቱም የተለየ ነጠላ ታሪካዊ ሁነት - ተዓምር - ስለነበር።ከሰዎች ሌላ ሕይወት ያላቸው ፍጡራንን በተመለከተ የእስልምና ምንጮች ዝምተኛ ሲሆኑ አላህ፥ በዝግመተ ለውጥም ሆነ በሌላ፥ እሱ በፈለገው መንገድ የፈጠራቸው መሆኑን ብቻ እንድናምን ይጠይቁናል።
ሙስሊም ስለ ሕይወት ያለው እይታ
እኔ የተቀደሰ ዓላማ አለኝ
በአላህ ምሕረት ተስፋ እና በቅጣቱ ፍርሃት መካከል ሚዛናዊነት
መልካም ነገር ሲገጥምህ አመስግን። ክፉ ነገር ሲገጥምህ ደግሞ ታገስ
እምነቴን በአላህ ላይ ማድረግ - በእሱ ፈቃድ እንጂ ምንም ነገር አይከሰትም
ይህ ሕይወት ፈተና ሲሆን የምሰራውን ነገር ሁሉ አላህ ይመለከታል
ያለኝ ነገር ሁሉ ከአላህ ነው
ትኩረቴን እኔ በምቆጣጠረው ነገር ላይ አድርጌ የቻልኩትን ያህል መሞከር
ከእስልምና ውጪ ያሉ መመራትን ያገኙ ዘንድ ከልብ ማሰብና ተስፋ ማድረግ
ወደ አላህ ተመላሽ ስሆን በስራዬም እጠየቃለሁ
