እስልምና የፅንፈኝነት ሐይማኖት አይደለም። الإسلام والتطرف

3.48 MB 56 1 Files
albyan
or download free
[free_download_btn]

Description

አላህ እንዲህ ይላል፦

“… ንፁህ ነፍስን የገደለ ሰው ሰዎቹን ሁሉ እንደገደለ ነው፤ ሕያው ያደረጋትም ሰው ሰዎቹን ሁሉ ሕያው እንዳደረገ ነው፡፡…” ቁርዓን 5፡32

መሠረታዊያኑን ይማሩ

እስልምና... ፅንፈኛ ሃይማኖት?

"ኢስላማዊ አሸባሪዎች!" "ሙስሊም አክራሪዎች!" "ፅንፈኞች!" "አክራሪ ኢስላሚስቶች!"

እነዚህ ከብዙ በጥቂቱ ሙስሊሞችን እና የተወሰኑ ሙስሊም ቡድኖችን ለመግለፅ በቅርብ አመታት ውስጥ በተሳሳተ መንገድ ጥቅም ላይ የዋሉ የስም ልጠፋዎች ናቸው።

የመገናኛ ብዙሃን እስልምናን የሚስሉበት መንገድ ስለሐይማኖቱ ያላቸው ግንዛቤ ውሱን የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብዙውን ጊዜ በተሳሳተ መንገድ ስለዚህ በጣም ሰላማዊና መቻቻልን የሚያስቀድም የህይወት ዘይቤ አሉታዊ ግምቶች እንዲወስዱ የሚያደርግ ነው።

ከ30 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት ያገለገሉት ፒተር ማኒንግ፥ "እኛ እና እነርሱ" በሚለው መጽሐፋቸው ይህን ገልፀዋል፦

“የህይወት ተሞክሮዬ እንደሚነግረኝ፥ በአረባዊና ሙስሊም አውስትራሊያናዊያን የዕለት ከዕለት ህይወት እውነታዎች እና በእኛ [የአውስትራሊያ] ብዙሃን መገናኛ በሚሰጣቸው ሽፋን መካከል እጅግ ሰፊ ልዩነት አለ።

ከ60 በመቶ በሚበልጡ ኬዞች [በሁለት አበይት ጋዜጦች ሽፋን]፥ ‘በአደጋ የተሞላ’፣ ‘ሞት’፣ ‘ጥቃት’፣ ‘መግደል’፣ ‘አጥፍቶ መጥፋት’ ወይም ‘ታጣቂዎች’ የሚሉት ቃላት ‘አረብ’፣ ‘ፍልስጤማዊ’፣ ‘ሙስሊም’ ወይም ‘እስልምና’ ከሚሉት ቃላት በጣም በቅርበት ነበር የተገኙት።

እናስ ታዲያ፥ ብዙ ሰዎች እስልምናን ከአሸባሪነት ጋር ቢያይዙት ምኑ ይገርማል?

የግንዛቤ እጥረት ችግር ስለመኖሩ ከሶስት አውስትራሊያዊያን መካከል ከአንድ በላይ የሚሆኑት ስለእስልምናም ሆነ ስለተከታዮቹ ምንም ነገር እንደማያውቁ ማመናቸውን ባጋለጠ አንድ የዳሰሳ ጥናት አማካይነት ተወስቷል።

“ከሙስሊሞች ጋር በጣም አነስተኛ ትውውቅና በጣም ዝቅተኛ ግላዊ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ነበሩ በእስልምና ይበልጥ ስጋት የሚያድርባቸው” ብለዋል ዶ/ር ዱን፥

ይህንን ጥናት እንዲያደርጉ በአውስትራሊያ-ኢንዶኔዥያ ኢንስቲትዩት የተመረጡት ምሁር።

የብዙሃን መገናኛ እስልምናን የተመለከተ የኢሚዛናዊነትና የግዴለሽነት መንሰራፋት እስልምናን በተገቢው አስተምህሮቶቹ በኩል በመረዳት ሊገታ ይችላል።

ይህም ማለት ቁርዓንን (የፈጣሪ ቃል እንደሆነ ሙስሊሞች የሚያምኑበት መፅሃፍ) እና የነብዩ ሙሐመድን (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ትክክለኛ ንግግሮች (ሶሂህ ሐዲሶች) በማጣቀስ ማለት ነው።

እነዚህን አስተምህሮቶች በተገቢው መንገድ በመረዳት፥ አንድ ሰው እስልምና ከየትኛውም አይነት ፅንፈኝነት በተቃራኒው መሆኑን ይደርስበታል።

ቁርዓን እንዴት በተሳሳተ መንገድ ሊወሰድ እንደሚችል

አንድ ሰው ቁርዓንን ወይም የነቢዩ ሙሐመድ (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ሐዲሶችን በሚያነብ ጊዜ፥ ቃላቱ የገቡበትን አውድ መገንዘብ አለበት።

የሚከተለው የቁርዓን አንቀፅ ስለእስልምና ሰዎችን ለማሳሳት በሚፈልጉ አካላት ዘንድ ተወዳጁ ነው፥

"ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው። ከአወጧችሁም ስፍራ አውጧቸው። መከራም ከመግደል ይበልጥ የበረታች ናት። በተከበረው መስጊድም ዘንድ በርሱ ውስጥ እስከሚጋደሏችሁ ድረስ አትጋደሏቸው። ቢጋደሏችሁም ግደሏቸው፤ የከሓዲዎች ቅጣት እንደዚህ ነው።” ቁርዓን 2፡191

አንዳንድ ጊዜያት፥ ይህ አንቀጽ በአደገኛ ሁኔታ እንደሚከተለው ተከርክሞ ይቀርባል፤

"ባገኛችኋቸውም ስፍራ ሁሉ ግደሏቸው።..." ቁርዓን 2፡191

ግልፁ ጥያቄ ማንን ነው “ግደሉ" የተባለው? ይህን ጥያቄ ለመመለስ፥ አንድ ሰው ከአንቀፅ 2፡191 በፊት ቀድመው የሚመጡትንና ቀጥለው ያሉትን አንቀፆች ማንበብ ይኖርበታል።

"እነዚያንም የሚጋደሏችሁን (ከሓዲዎች) በአላህ መንገድ ተጋደሉ። ወሰንንም አትለፉ፤ አላህ ወሰን አላፊዎችን አይወድምና።" ቁርአን 2፡190

የላይኛው አንቀጽ መጋደልን ራስን እንደመከላከል (ማለትም የተጋደሏችሁን) አድርጎ ነው የጠቀሰው።

ከ2፡191 ቀጥሎ ያለው አንቀጽ፦

"ቢከለከሉም አላህ መሓሪ አዛኝ ነው።" ቁርዓን 2፡192

እነዚህ አንቀጾች ሙስሊሞች በእምነታቸው ምክንያት ከቤቶቻቸው በጉልበት እንዲወጡ በተደረጉበት ጊዜ ነበር የወረዱት።

ከአሥር ዓመታት በላይ ሲደርስባቸው የነበረውን ግፍ ችለው በመጨረሻም ደህንነቱ ወደተጠበቀ ስፍራ መሰደድ ነበረባቸው።

ከላይ የተጠቀሱት አንቀፆች በነቢዩ ዘመን የነበሩ ሙስሊሞችን የጨቆኑ እና ሙስሊሞች ጥገኝነት በጠየቁበት ስፍራ ሁሉ ሄደው ሊያጠቋቸው ያቅዱ የነበሩ የመካ ጣዖት አምላኪ አረቦችን ነበር የሚያመለክቱት።

ስለዚህ፣ ከላይ ያለው አንቀጽ ይህን በመሰሉ ሁኔታዎች ብቻ ነው ሊገባ የሚችለው።

ይህ ምሳሌ የቁርዓን አናቅፅትን በተገቢው አውዳቸው ልንረዳቸው እንደሚገባ ያሳያል።

ምክንያቱም አንቀጾች፥ በ23 ዓመታት ውስጥ፥ ይገለጡ የነበሩት ከሆኑ የተለዩ ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ስለነበር ነው።

እንዲሁም ቁርዓን በአረቢኛ ቋንቋ እንደወረደ ማስታወስ አስፈላጊ ነው።

ስለዚህ፥ ወደተለያዩ ቋንቋዎች መተርጎም ሊያሳስት እና/ወይም ሊያጣምም ይችላል።

የሚፈቀድ ፍልሚያ/ተጋድሎ

ሙስሊሞች (እንደማንኛውም ማህበረሰብ) ሲወረሩ አልያም ጭቆና ሲደርስባቸው የመፋለም መብት ያላቸው መሆኑ ጥርጥር የለውም።

የማኅበረሰብ ደህንነትን ለማስጠበቅ፣ የጭቆና መስፋፋትን ለመከላከል ውጊያ እንደሚፈቀድ እስልምና ያስተምራል፤ ይህም ልዩ ሁኔታው እንደሚፈቅደው በመከላከል መለክ አልያም በማጥቃት መልክ ሊከናወን ይችላል።

እስልምና፥ እንደማንኛውም ዘላቂነቱን ማረጋገጥ እንደሚፈልግ ‘የህይወት መንገድ‘ ሁሉ፥ ጦርነት ሲታወጅበት ራሱን የመከላከል መብት አለው።

በቁርዓን (22፡39) ውስጥ ይህን እናነባለን፦

"ለእነዚያ ለሚጋደሉት (ምእመናን) እነርሱ የተበደሉ በመሆናቸው (መጋደል) ተፈቀደላቸው።"

ነገር ግን፥ ጠላት ፀበኛነቱን ሲተው፥ ሙስሊሞችም መዋጋታቸውን እንዲያቆሙ ታዘዋል።

"ወደ ዕርቅም ቢያዘነብሉ ወደ እርሷ አዘንብል። በአላህም ላይ ተጠጋ። እነሆ እርሱ ሰሚ ዐዋቂ ነውና።" ቁርዓን 8፡61

አቡ በከር (ስራቸውን አላህ ይውደድላቸው)፥ የነቢዩ ሙሐመድ የቅርብ ወዳጅና የመጀመሪያ ኸሊፋ፥ የሚከተሉትን ነጥቦች በማጉላት ስለኢስላማዊ የጦርነት አግባብ ተናግረዋል፤

በጦር ሜዳ አንድ ሰው ይህን ማድረግ የለበትም፦

· ክህደት መፈፀም

· የሟቾችን አካል መቆራረጥ

· ከትክክለኛው መንገድ ማፈንገጥ

· ሴቶችን፣ ህፃናትን ወይም አረጋዊያንን መግደል

· ዛፎችን መጉዳት ወይም ማቃጠል፥ በተለይ ፍሬ ያላቸውን

· የጠላትን እንስሳት ለምግብ ከሚፈለገው ውጪ ማረድ

· ሕይወታቸውን ለአምልኮ የሰጡ ቅዱስ ሰዎችን መጉዳት

በአንቀጽ 2፡190 እንዳነበብነው፥ ወደፅንፍ እንዳይሄዱ አላህ ሙስሊሞችን እንዲህ ሲል ያዛል፥፦ "ድንበርን አትለፉ።"

ድንበርን ለማለፍ የጦርነት ሁኔታ ሰበብ አይሆንም።

ጭፍን የበቀል ጥቃት ማስወገድን እስልምና ያስተምራል።

"ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ። አስተካክሉ። እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው።" ቁርዓን 5፡8

ሽብርተኝነት አንፃር በአንፃር

ሽብርተኝነትን አንፃር በአንፃር ማየትን አስቸጋሪ የሚያደርገው "ሽብርተኝነት" ምን እንደሆነ የሚገልፅ ሁሉን የሚያስማማ ብያኔ የሌለ መሆኑ ነው።

እንዲሁም የሚከተሉት ምሳሌዎች እንደሚያሳዩት ሽብርተኝነት የተለያዩ መልኮችን ይወስዳል።

የዘ ኢንዲፔንደንቱ ሮበርት ፊስክ እንዲህ ፅፏል፦

"እስራኤልና የእስራኤል የሚሊሻ አጋሮች (በሴፕቴምበር 16 1982) በሳብራና ሻቲላ የፍልስጤማውያን ስደተኞች ካምፖች ላይ ለሶስት ቀናት የቆየና 1,800 ሰዎችን የበላ የጅምላ አስገድዶ መድፈር፣ የስለት ጥቃት እና የግድያ ጥቃታቸውን ጀመሩ። በአሜሪካ አረንጓዴ መብራት ተበርቶላት ፒ ኤል ኦን (የፍልስጤም ነፃነት ግምባር) ከአገሪቱ ለማስወጣት አልማ እስራኤል ሊባኖስ ላይ የፈፀመችውን ወረራ ተከትሎ የተፈፀመ ነው። ይህም የ17,500 ንፁሃን የሊባኖስና የፍልስጤም ዜጎችን ህይወት አጥፍቷል።”

እንደ ፕሮፌሰር ኖአም ቾምስኪ አባባል፦ “አሜሪካን ግምባር ቀደም አሸባሪ አገር ለመሆኗ ብዙም አያጨቃጭቅም። እንዲያውም በከፍተኛዎቹ አካላት፡ የአለማቀፉ የፍትህ ሸንጎ (አይ ሲ ጄ) በ1986 በአለማቀፍ ሽብርተኝነቷ የተወገዘች ብቸኛዋ አገር ነበረች።”

በተመሳሳይም፥ “በ1995 በስሬብሬኒካ በ8000 ሙስሊሞች ላይ - አንዳንዶቹ ምንም ያልታጠቁ - የተፈፀመው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ክርስትና ውስጥ ስላለው የአደገኛነትና የጨቋኝነት አዝማሚያ የሚዲያ ዘገባ ጋጋታን ፈፅሞ አላስከተለም።” ዊልያም ዳልሪምፕል፣ ዘ ኢንዲፔንደንት ዩኬ

"ባለፉት 60 ዓመታት ውስጥ ምዕራባዊያን፥ ላይ ላዩን ክርስቲያናዊ፥ መሪዎች የፈጠሩት እልቂት - የዓለምና ቀዝቃዛ ጦርነቶች፣ ሆሎኮስት፣ ሁለት የአቶም ቦምቦ ጥቃቶች፣ የነፃነት ትግል አፈናዎች፣ ፕሮክሲ ጦርነቶችን ማቀጣጠል፣ የኒውክሌር ግብግብ፣ አምባገነኖችን እና ብሄራዊም ብሄራዊ ያልሆኑም ሽብርተኞች ድጋፍን ጨምሮ፥ እስልምናን ይበልጥ አደገኛነት የተጠናወተው ሐይማኖት ወይም ስልጣኔ አድርጎ የመውሰዱን ነገር ቀልድ ያደርገዋል።" - ራማ ማኒ (የጄኔቫ የደህንነት ፖሊሲ ማዕከል)

ሌሎች ብዙ የይሁዲ እና የክርስትና ሽብርተኝነት ምሳሌዎች ቢኖሩም፥ ሁሉንም ይሁዲዎች እና ክርስቲያኖች ባጠቃላይ አሸባሪዎች ብለን ፈፅሞ መጥራት ግን የለብንም።

እስልምና ሽብርተኝነትን ያወግዛል

ምንም የማያውቁ ሰላማዊ ሰዎች ልብ ውስጥ ሽብርን የመንዛት ተግባር፣ ተቋማትንና ንብረትን በጅምላ ማውደም፣ በንጹሃን ወንዶች፣ ሴቶችና ህጻናት ላይ የቦምብ ጥቃትና የአካል ጉዳት ማድረስ ሁሉም ክልክል ከመሆናቸው ባሻገር በእስልምናም ሆነ በሙስሊሞች ዘንድ የሚጠሉ ፀያፍ ድርጊቶች ናቸው።

ይህ የትኛውንም አይነት ሽብርተኝነት የሚመለከት ነው - ከሌሎች ሁሉም የሽብርተኝነት አይነቶች ይበልጥ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ሰዎችን የገደለውን፣ ያቆሰለውን እና ያፈናቀለውን በምዕራባዊ መንግስታት ስፖንሰር የሚደረገውን ሽብርተኝነት ጨምሮ።

አንድ ሙስሊም የሽብርተኝነት ድርጊት ቢፈጽም፥ ይህ ሰው እከተለዋለሁ የሚለውን ሐይማኖት፥ እስልምና፥ ቀኖናዎች በመጣስ ሐጢዓት ውስጥ ይገባል።

ሐይማኖቱ ራሱ እንዲህ አይነት ድርጊቶችን የሚቃረን ሆኖ ሳለ፥ በዚህ የተነሳ ሁሉንም ሙስሊሞች ማውገዝ ሚዛናዊ ይሆናልን?

ሙስሊሞች ለአላህ የመገዛት፣ የሰላም፣ የእዝነት፣ እና የይቅርታ ሃይማኖትን ይከተላሉ።

እጅግ ሰፊው የሐይማኖት ተከታዮች አንዳንዶች – ለአብነት ያህል ብዙሃን መገናኛው - ከሙስሊሞች ጋር በሚያዛምዷቸው የጥፋት ድርጊቶች ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም።

እስልምና የፅንፈኝነት ሃይማኖት አይደለም።

"ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ (ከሓዲዎች) መልካም ብትውሉላቸውና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም። አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና።" ቁርዓን 60፡8

Similar Downloads

No related download found!