ኢየሱስ፡ የአላህ ነቢይ عيسى في الإسلام

8.31 MB 65 1 Files
albyan
or download free
[free_download_btn]

Description

ኢየሱስ፡ የአላህ ነቢይ

ሙስሊሞች ኢየሱስን ይወዳሉ

ኢየሱስ በመላው አለም በቢሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች የሚወደዱና የሚታፈሩ ሰው ናቸው፤ ሆኖም ግን የእኚህ ታላቅ ሰው ድረጃ በብዙ ውዝግቦች ተከቧል።

ሙስሊሞችም ክርስቲያኖችም ለኢየሱስ ከፍተኛ አክብሮት አላቸው፤ ግን እሳቸውን በጣም በተለያዩ መንገዶች ነው የሚያዩዋቸው።

ይህ በራሪ ወረቀት በኢየሱስ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን ግልፅ ለማድረግ ያልማል፥ ኢየሱስ አምላክ ነበሩን? ወይስ በአምላክ የተላኩ ናቸው? በታሪክ የሚታወቁት የእውነቱ ኢየሱስ ማን ነበሩ?

ኢየሱስ እንደ አምላክ

አንዳንድ ክርስቲያኖች "ኢየሱስ አምላክ ነው" ወይም የስላሴ አካል ነው - ምድር ላይ የአምላክ ምትክ፥ እና አምላክ በሰው ተመስሎ - ይላሉ።

ነገር ግን፥ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው ከሆነ ኢየሱስ ተወልዷል፤ ይበላና ይተኛ ነበር፤ ይፀልይ ነበር፤ ውስን እውቀትም ነበረው – ሁሉም አምላክን የማይመጥኑ ባህሪያት።

አምላክ ያሉት ባህሪያት ፍፁም ሲሆኑ፥ የሰው ግን በተቃራኒው ነው። የትኛውም ነገር እንዴት በአንድ ጊዜ ሁለት ፍፁም የሚቃረኑ ነገሮችን ሊሆን ይችላል?

አምላክ ሁልጊዜም ፍጹም መሆኑን እስልምና ያስተምራል።

አምላክ ሰው ሆነ ብሎ ማመን፥ አምላክ (የሆነ ጊዜ ላይ) ኢፍፁም ነው/ነበር እንደማለት ነው።

አንድ/ዲት ክርስቲያን ራሱን/ሷን መጠየቅ ይኖርበታል/ባታል፤ በአንድ ወቅት ያለምግብ፣ ያለመጠጥና ያለእንቅልፍ መኖር የማይችል ደካማ አቅመ ቢስ የነበረ ጨቅላ የአምላክነት ሐሳብ፥ እውን ያ በብሉይ ኪዳን የተገለፀው ተመሳሳይ ሐያል አምላክ ነው?

በእርግጠኛነት አይደለም።

"አምላክ ማንኛውንም ነገር ማድረግ እስከቻለ ድረስ፥ ለምን ሰው መሆንስ አይችልም?" ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል።

በመርህ ደረጃ፥ አምላካዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን አምላክ አያደርግም።

ከአምላክነት ውጪ ሌላ ነገር ሊያሰኙት የሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች አምላክ አይሰራም።

አምላክ ሰው ቢሆንና ሰዋዊ ባህሪያትን ቢላበስ፥ ከዚያ ኋላ አምላክነቱ የግድ ይቆም ነበር።

ኢየሱስ በሆነ መንገድ መለኮታዊ መሆኑን ለማሳየት አንዳንድ አሻሚነት ያላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አንቀፆች ሊመዘዙ ይችላሉ።

ነገር ግን፥ ግልጽና ቀጥተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ አንቀፆችን ከተመለከትን ኢየሱስ እጅግ ምርጥ የሰው ልጅ እንጂ ሌላ ምንም አለመሆኑን ደግመን ደጋግመን እናያለን።

አምላክ ከእርሱ የተለየ አካል እንደሆነ አድርጎ ኢየሱስ የሚናገርባቸው እና ባህሪውን የሚገልፅባቸው በርካታ አንቀፆችን መፅሐፍ ቅዱስ ይዟል። ለምሳሌ፡

• ኢየሱስ "በግምባሩ ወደቀና ጸለየ።" [ማቴዎስ 26፡39] ኢየሱስ አምላክ ከነበረ፥ ታዲያ አምላክ የሆነ አካል በግምባሩ ወደቆ ሊፀልይ ይገባዋልን? እና የሚፀልየውስ ለማን ሊሆን ይችላል?

• መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን ነቢይ ብሎ ይጠራዋል [ማቴዎስ 21፡10-11]፤ ስለዚህ እንዴት ነው ኢየሱስ በአንድ ሰዓት አምላክ እና ነቢይ ሊሆን የሚችለው?

• ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ "እኔ ወደ አባቴ እሄዳለሁ፤ ምክንያቱም አባቴ ከእኔ ይልቅ ታላቅ ነው።" [ዮሐንስ 14፡28]

• ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ "ወደ አባቴና አባታችሁ፣ ወደ አምላኬና አምላካችሁ አርጋለሁ።" [ዮሐንስ 20፡17] ኢየሱስ አምላክ ከሆነ፥ ታዲያ ለምን "ወደ አምላኬና አምላካችሁ" ይላል? ደግሞስ የሚያርገው ወደ ማን ነው?

ኢየሱስ አምላክ ቢሆን ኖሮ፥ በግልጽ ሰዎችን እንዲያመልኩት ይናገር ነበር፤ እናም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደዚህ የሚሉ ግልጽ አንቀፆች ይኖሩ ነበር፤ ነገር ግን እርሱ ተቃራኒውን በማድረግ የሚያመልከውን ማንኛውም ሰው ኮንኗል።

"በከንቱ ያመልኩኛል።" [ማቴዎስ 15፡9]

"የአምላክ ልጅ"

አንዳንድ ክርስቲያኖች ኢየሱስ የአምላክ ልጅ እንደሆነ ይናገራሉ። ይህ በተግባር ምን ማለት ነው?

እርግጥ ነው አምላክ አካላዊም ሆነ ቃላዊ ልጅ ያለው ከመሆን እጅግ የራቀ ነው። የሰው ልጆች ሰው የሆኑ ህፃናት ይኖሯቸዋል። ድመቶች ግልገል ይኖራቸዋል። አምላክ ልጅ አለው ሲባል ምን ማለት ነው?

በቃላዊ ፍቹ ከመወሰድ ይልቅ፥ "የአምላክ ልጅ" የሚለውን አገላለፅ በጥንታዊያኑ የመፅሃፍ ቅዱስ ቋንቋዎች - ለኢየሱስ ለብቻው ሳይሆን - ለብዙ “አምላክን ፈሪ” ሐይማኖተኛ ሰዎች -

ለእነ ዳዊት፣ ሰለሞን እና እስራኤል ጥቅም ላይ እንደዋለው - በተምሳሌታዊ መገለጫነት ጥቅም ላይ ሲውል እናገኛለን፤ “. . . እስራኤል የበኩር ልጄ ነው፤” [ዘጸአት 4፡22]

**በእውነት፣ ማንኛውም ጻድቅ እንደ "እግዚአብሔር ልጅ" ይጠቀማል። "በአላህ መንፈስ የተመራና ያለው ማንኛውም ሰው፣ እርሱ

"አላህ ልጅ እንዲያወልድ የሚገባው አይደለም። እርሱ ፍጹምና ነፍሰጻድቅ ነው። አንደኛን ነገር ቢያስቀምጥ፣ እርሱ የሚለው፣ 'ሁን!' እና እሱም ይሆናል።" - ቁርአን 19፡35

"አባት እና ጌታ"

በተመሳሳይ መንገድ፥ "አባት" የሚለው ቃል አምላክን ለመግለፅ ጥቅም ላይ ሲውል፥ ቃል በቃል መወሰድ የለበትም።

ይልቁንስ፥ አምላክ ፈጣሪ፣ ረዛቂ እና የሁሉም የበላይ አዛዥ መሆኑን የሚገልፅ አጠቃቀም ነው።

"አባት" የሚለው ቃል ያለውን ይህን ተምሳሌታዊ ፍቺ ለመረዳት በርካታ አንቀፆች አሉልን፤ ለምሳሌ፦ "የሁሉም አባት የሆነ አንድ አምላክ" [ኤፌሶን 4፡6]

እንዲሁም፥ ኢየሱስ አንዳንድ ጊዜ በደቀ መዛሙርቱ "ጌታ" እየተባለ ይጠራ ነበር።

ቃሉ በመጀመሪያዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋዎች ጥቅም ላይ የዋለው ለአምላክም ከፍተኛ ክብር ለሚሰጣቸው ሰዎችም ባንድ ነው።

ለምሳሌ፥ የግሪኩ ሐዲስ ኪዳን ውስጥ፣ "ኪሪዮስ" የሚለው ቃል "ጌታ"ን እና የወይን አትክልት ባለቤቱን (ማቴዎስ 20፡8)፥ እንዲሁም እምቢተኛውን አገልጋይ የገረፈውን አዛዥ (ሉቃስ 20.42-47) ለመጥራት ጥቅም ላይ ውሏል።

በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፥ ኢየሱስ በደቀ መዛሙርቱ ጭራሽ የአምላክ "ባሪያ" ተብሎ ተጠርቷል፦ "የአባቶቻችን አምላክ ባሪያውን ኢየሱስን አከበረው።" [የሐዋርያት ሥራ 3፡13]

"ጌታ" የሚለው ቃል ኢየሱስን ለማመልከት ጥቅም ላይ ሲውል የአክብሮት ማዕረግ እንጂ የመለኮታዊነት አለመሆኑን ይህ በግልጽ ያሳያል።

ከላይ የተጠቀሱትን የአምላክን ባህሪ እና የኢየሱስን ተፈጥሮ የተመለከቱ ጉዳዮችን ውስብስብነት ለማብራራት ሙከራዎች ተደርገዋል፤ ይህም በጣም የሚያደናግር እና የማያረካ ሊሆን ይችላል።

ነገር ግን፥ ሊውጠነጠን የሚገባው ቁልፍ ነጥብ፦ጉዳዩን አምላክ ለምን ይህን ያህል ለመገንዘብ አስቸጋሪ አደረገው?

እነዚህ ውስብስብ አስተምህሮቶች ቀላል፣ ግልጽና ንፁህ ከሆነው ከኢስላማዊው የአምላክ ፅንሰ ሐሳብ አስተምህሮ ጋር እንዴት ይነፃፀራሉ?

ኢየሱስ፦ ነቢዩ

ኢየሱስ (ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን) በይሁዲ እምነት መሲህነቱ ተክዷል።

ይህ በክርስትና ውስጥ ካለው እንደጣዖት አልያም እንደአምላክ ልጅ የመመለክ ደርጃው ጋር በከባዱ የሚቃረን ነው።

እስልምና መካከለኛውን መንገድ በመያዝ ኢየሱስን እንደተከበረ ነቢይና የአላህ መልእክተኛ፥ እንዲሁም እንደ መሲህ ይቀበላል።

ነገር ግን ሙስሊሞች እሳቸውን አያመልኩም - ምክንያቱም አምልኮ የሚገባው ኢየሱስንም ሆነ ሌላውን ነገር ሁሉ ለፈጠረው አንድዬ አምላክ ብቻ ነውና።

"(ሕፃኑ ኢሳም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡»'" - ቁርአን 19፡30

ተዓምራዊ ውልደት

ቅዱስ ቁርዓን እንደሚለው፥ መልዓኩ ገብርኤል በሰው ተመስሎ፥ ወደተከበረችው ድንግል፥ ወደማርያም ተላከና ያለአባት በተዓምር ስለምትወልደውም ልጅ አበሰራት።

“«እኔ ንጹሕን ልጅ ለአንቺ ልሰጥሽ የጌታሽ መልክተኛ ነኝ» አላት።

«(በጋብቻ) ሰው ያልነካኝ ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች።

አላት «(ነገሩ) እንደዚህሽ ነው።» ጌታሽ «እርሱ በእኔ ላይ ገር ነው። ለሰዎችም ተዓምር ከእኛም ችሮታ ልናደርገው (ይህንን ሠራን) የተፈረደም ነገር ነው» አለ፤ (ነፋባትም)።” - ቁርዓን 19፡19-21

አንዳንዶች የኢየሱስን ተዓምራዊ ውልደት መለኮታዊነቱን አስረጅ መሆኑን ይናገራሉ።

ነገር ግን፥ ኢየሱስ ያለአባት በመገኘት የመጀመሪያው አይደሉም፤ ከእርሱ በፊት ነቢዩ አዳም (ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) አባትም ሆነ እናት አልነበራቸውምና።አላህ እንዲህ ይላል፦

"አላህ ዘንድ የዒሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው። ከዐፈር ፈጠረው። ከዚያም ለእርሱ (ሰው) «ሁን» አለው፤ ሆነም።

ይህ ከጌታህ ዘንድ የሆነ እውነት ነው። ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን።" - ቁርዓን 3፡59-60

ኢየሱስ ያለአባት በመፈጠሩ ምክንያት ከተመለከ፣ ያለሁለቱም ወላጆች የተፈጠሩት አደምማ በእርግጠኛነት ይበልጥ መመለክ ይገባቸዋል።

የኢየሱስ ተዓምራት

ኢየሱስ ያለ አባት በተዓምራዊ ሁኔታ ነበር የተፀነሰው፤ እናም በተጨማሪ በአላህ ፈቃድና ይሁንታ ታላላቅ ተዓምራትን ፈፅሟል።

ሰዎች በእናቱ ላይ የቃጡትን የአመንዝራነት ውንጀላ ለመከላከል ህፃን ሆኖ ሳለ ገና በጨቅላነቱ ተናግሯል።

በተጨማሪም ኢየሱስ ሙታን ማስነሳቱን፣ ደዌ የለከፈውንና አይነ ስውርን መፈወሱን - ሁሉም በአላህ ፈቃድ - ቁርአን ያትታል።

ኢየሱስ (ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን) ተዓምራትን የመፈፀሙ እውነታ ትሁት የአላህ አገልጋይ የነበረ ከመሆኑ ውጪ ሌላ ነገር ማለት አይደለም።

በእርግጥ፥ ኖኅ፣ ሙሴ እና መሐመድን (ሰላም በሁላቸውም ላይ ይሁን) ጨምሮ ብዙ መልእክተኞች ተዓምራት ፈፅመዋል፤

እናም እነዚህ ተዓምራት ሊፈፀሙ የቻሉት አላህ ስለፈቀደ ብቻ ነው፤ የመልዕክተኛውን እውነተኛነት ለማሳየት ሲባል።

የኢየሱስ መልዕክት

እንደ አብርሃም፣ ኖኅ፣ እና ዮናስ የመሳሰሉት የብሉይ ኪዳን ነብያት አምላክ አምላክ የስላሴ አካል ነው ብለው መቼም ሰብከው አያውቁም፤ ኢየሱስም አዳኛችን ነው ብለው አላመኑም።

መልእክታቸው ቀላል ነበር፦ ያለው አንድ አምላክ ሲሆን አምልኳችሁም ለእርሱ ብቻ የተገባ ነው።

አምላክ ለሽህዎች ዘመናት በመሰረታዊነት ከሚመሳሰል መልዕክት ጋር ነብያትን ሲልክ ቆይቶ፥ ከዚያም በቃ አሁን የስላሴ አካል ነኝ ብሎ በድንገት መቀየሩ ምክንያታዊ (ሎጂካል) አይደለም፤

እንዲሁም ለመዳን በኢየሱስ መለኮታዊነት ማመንን መደንገግ (ምክንያታዊ አይደለም)።

እውነቱ ምንድነው፥ እንደሁሉም የብሉይ ኪዳን ነቢያት ኢየሱስም የሰበከው ተመሳሳይ መልዕክትን ነው።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህንን ወሳኝ መልእክት የእውነትም አበክሮ የሚያሳይ ምንባብ አለ።

አንድ ሰው ወደ ኢየሱስ መጥቶ “ለመሆኑ ከትዕዛዛት ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ነው?” ሲል ጠየቀው

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እስራኤል ሆይ ስማ፥ ጌታ አምላካችን አንድ ጌታ ነው።” [ማርቆስ 12፡28-29]

ስለዚህ፥ እንደ ኢየሱስ እይታ እጅግ ወሳኙ እምነት፥ እጅግ ታላቁ ትዕዛዝ፥ አምላክ አንድ መሆኑ ነው።

ኢየሱስ አምላክን ቢሆን ኖሮ፥ “እኔ አምላክ ነኝ፣ አምልኩኝ” ይል ነበር።

ከዚያ ይልቅ፥ አምላክ አንድ እንደሆነ የሚያረጋግጥን የብሉይ ኪዳን አንድ አንቀፅ ነው እንደዋዛ የደገመው።

ይህ፥ ኢየሱስ ወደእስራኤል ልጆች የተላከው የቀደሙ ነቢያትን መልዕክት ለማረጋገጥ እንደነበር እስልምና እንደሚያስተምረው፥ ከኢየሱስ ተልዕኮ – በአንዱ እውነተኛ አምላክ ማመን – ጋር የሰመረ ነው።

"ዒሳ በታምራቶች በመጣ ጊዜም አላቸው ‘ . . . በእርግጥ አላህ ጌታዬ ጌታችሁም ነውና ተገዙት። ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነው።’" - ቁርዓን 43፡63-64

እንደተከበረ ታዛዥ የአላህ መልእክተኛ፥ ኢየሱስ የአላህን ትእዛዛት በውዴታ ተቀብሏል።

በዚህም የተነሳ፥ እርሱ "ሙስሊም" ነበር – ለአላህ ፈቃድ እና ትዕዛዛት ያደረ ማንኛውም ሰው ሙስሊም በመባል ስለሚታወቅ።

ኢየሱስ በእስልምና

ኢየሱስ አላህን በብቸኝነት ማምለክን እንዲጣራ በአላህ የተላከ የተከበረ ነቢይ ነበር።

ይህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጨባጭ የተጠቀሰ ሲሆን በቁርዓንም የተረጋገጠ ነው።

ኢየሱስን በተመለከተ ኢስላማዊው እምነት እውነተኛው ኢየሱስ ማን እንደነበር ያብራራል።

ስለ አላህ እና ስለ ፍፁም ታላቅነቱ፣ ብጤ የለሽነቱ እና ምሉዕነቱ ንፁህ የሆነው እምነት እንደተጠበቀ ሳለ።

እርስዎ በተጨማሪ አልፈው በመሄድ እስልምናን እንዲመረምሩ እንጋብዞታለን። ዝም ብሎ ሌላ ተራ ሐይማኖት አይምሰልዎ።

በኖኅ፣ በአብርሃም፣ በሙሴ፣ በኢየሱስ እና በመሐመድ - ሰላም በሁላቸውም ላይ ይሁን - የተሰበከው ተመሳሳይ መልዕክት ነው።

እስልምና ማለት “ለአላህ ማደር” ማለት ሲሆን ተፈጥሯዊና የተሟላ የህይወት መንገድ ነው።

ሰዎች ከአላህ እና ከእርሱ ፍጥረተ ዓለም ጋር ላላቸው መስተጋብር የሚገባውን ትኩረት እንዲሰጡ ያበረታታል።

አላህ እጅግ ፍትሃዊ እና እጅግ አዛኝ መሆኑን እስልምና ያስተምራል።

እናም ኃጢአትን ለማስተስረይ ሲል ራሱን መሠዋት አያስፈልገውም፤ ማንም ደግሞ “ኃጢአት ይዞ አልተወለደም”።

አላህ ሁሉንም ሰው ራሱ በሰራው ሥራ ላይ ተመስርቶ ነው የሚዳኘው፤ እናም እያንዳንዱ ሰው ራሱ በፈፀማቸው ተግባራት ነው የሚጠየቀው።

ሁሉንም የአላህ ነቢያት እንድንወድና እንድናከብር እስልምና ያስተምረናል።

ነገር ግን፥ እነርሱን መውደድና ማክበር ማምለክ ማለት አይደለም፤ ምክንያቱም አምልኮ ለአላህ ብቻ የተገባ ነውና።

ኢየሱስን እንደ አንድ የአላህ ነቢይ አምኖ መቀበል እና ሙስሊም መሆን ክርስቲያናዊ ማንነትዎን መቀየር አልያም ማጣት ማለት አይደለም።

ጉዳዩ እውነተኛና ንፁህ ወደሆኑት የኢየሱስ አስተምህሮቶች ስለመመለስ ነው።

Similar Downloads

No related download found!